Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፤ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች
1. የትምህርት መረጃ፡- ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት (2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት (2) ጉርድ ፎቶ ግራፍ
2. የድጋፍ ደብዳቤ፡- የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ የድጋፍ ደብዳቤ ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ Recommendation Letter/
3. የመመዝገቢያ ክፍያ፡- የማመልከቻ ክፊያ የ100 ብር ደረሰኝ በመያዝ የማመልከቻ ቅጽ ከቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና ከዩኒቨርሲቲው ድኀረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላሉ፡፡

በመንግሥት /በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመስሪያ ቤቱ/ በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም /Sponsorship Form/ ከዩኒቨርሲቲው ድኀረ-ገፅ (www.amu.edu.et) ማግኘት ይችላለ፡፡
የማመልከቻ፤ የፈተና መስጫ፤ የውጤት ማሳወቂያ፤ የምዝገባ ጊዜ እና ቦታ
የማመልከቻ ጊዜ፡- ከየካቲት 15/2014 ዓ.ም እስከ የካቲት 30/2014 ዓ.ም፤

የማመልከቻ ቦታ፡- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አ/ዳ/ጽ/ቤት ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና አዲስ አበባ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ጽ/ቤት አራት ኪሎ ሮሚና ካፌ ጎን፤
ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር የሚወጣበት ቀን፡- መጋቢት 02/2014 ዓ.ም፤ ለፈተና ያለፉ አመልካቾች ዝርዝር በውስጥ ማስታወቂያ እና በዩኒቨርሲቲው ድኅረ-ገጽ (www.amu.edu.et) መከታተል ይችላሉ፡፡

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን፡- መጋቢት 5/2014 ዓ.ም
ፈተና የሚሰጥበት ቦታ፡- የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ነጭ ሳር ካምፓስ
ማሳሰቢያ፡-
• ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ ብቻል በምዝገባ ወቅት ካልሆነ በ60 ቀናት ውስጥ ካልቀረበ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

• በአካል ቀርባችሁ ማመልከት ለማትችሉ አመልካቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂ/ቁ 1000021480502 የማይመለስ ብር የ 100 ገቢ ያደረጋችበትን አንድ ኮፒና ሙለ የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒ በማድረግ በ Email አድራሻችን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

• መደበኛ የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ሁሉም በተመጣጣኝ ክፊያ የዶርም አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

PhD Program - PhD in Public Health

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አ/ዳ/ጽ/ቤት