Print

ማኅበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ በ“ELT”፣ በ“Environment and Natural Resources Management” እና በ“Disaster Risk Management” ትምህርት ፕሮግራሞች በ3ኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ነገ ቅዳሜ ሰኔ/4/2014 ዓ/ም፣ የፊታችን ሰኞና ማክሰኞ ማለትም ሰኔ 6 እና 7/2014 ዓ/ም የመጨረሻ የምርምር ሥራቸውን የውጪና የሀገር ውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡

በዚህ መሠረት ዕጩ ዶ/ር ምኅረትዓብ አብረሃም በ “ELT PhD Program”፣ ቶማስ ቶማ በ “Disaster Risk Management PhD Program”፣ ታሪኩ ዘካሪያስ በ “Environment and Natural Resources Management PhD Program” እና ማሙሽ ማሻ በ “Environment and Natural Resources Management PhD Program” ያከናወኗቸውን የመመረቂያ ጽሑፎች ከላይ በተገለጸው መርሃ - ግብር የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡   ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫ

በተመሳሳይም የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ“Biodiversity Conservation and Management” ትምህርት ፕሮግራም በ3ኛ ዲግሪ ያሠለጠነው ዕጩ ዶ/ር ብርሃኑ ጌቦ የፊታችን ረቡዕ ሰኔ 8/2014 ዓ/ም “Socio-Ecological Drivers of Mammalian Diversity and Human-Carnivore Coexistence in the Faragosa-Fura Landscape of Southern Rift Valley, Ethiopia” በሚል ርዕስ የመመረቂያ ምርምር ሥራውን የውጪና የሀገር ውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት ያቀርባሉ፡፡

ዕጩ ዶክተሮቹ የምርምር ሥራዎቻቸውን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ቀደም ብለው የማሳተም ልምድ ያላቸው ሲሆን በዚህ መሠረት ዕጩ ዶክተር ምኅረትዓብ አብረሃም 3፣ ቶማስ ቶማ 3፣ ታሪኩ ዘካሪያስ 2፣ ማሙሽ ማሻ 3 እና ብርሃኑ ጌቦ 5 ጥናታዊ ጽሑፎችን ያሳተሙ ናቸው፡፡

ስለሆነም የሚመለከታችሁ የዘርፉ የ2ኛ ዲግሪና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎችና መምህራን በመርሃ-ግብሩ እንድትሳተፉ የተጋበዛችሁ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያስታውቃል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት