Print

በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂና ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቶች በምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎትና በኢንደስትሪ ትስስር ዘርፎች በተከለሰ መመሪያ ዙሪያ ሰኔ 25/2014 ዓ/ም ውይይት ተካሂዷል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በተከለሰው መመሪያ በምርምር፣ በማኅበረሰብ አገልግሎትና በኢንደስትሪ ትስስር የመምህራን ተሳትፎ ላይ ማሻሻያዎች መደረጋቸውን የዩኒቨርሲቲው የምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋዬ ሀብተማርያም ገልጸዋል፡፡ ዳይሬክተሩ ውይይቱ ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ አባል የሆነበትን የግራንት ሰርቺንግ ፕላትፎርም/Grant Searching Platform/ ለማስተዋወቅ እንዲሁም የምርምር ዩኒቨርሲቲን ምንነትና ከምርምር አንጻር ከእያንዳንዱ መምህር የሚጠበቀውን ለማስገንዘብ የተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ በመመሪያው በአምስቱ የምርምር ዓይነቶች፡- ‹‹Small Scale Research››፣ ‹‹Special Females Research››፣ ‹‹Grand Project›› እና ‹‹Young Research›› የገንዘብ አወጣጥ ሂደት ማሻሻያ እንደተደረገ ዶ/ር ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ሴዳ በበኩላቸው ዳይሬክቶሬቱ በዩኒቨርሲቲ-ኢንደስትሪ ትስስር፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሥራ ፈጠራና ልማት ማበልፀጊያ ማዕከል ሥራዎችን በሰፊው ለማከናወን በኮሌጆችና ኢንስቲትዩቶች አዳዲስ መዋቅሮች መዘርጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ፕ አዲሱ ሙሉጌታ መመሪያውን መገንዘብና ከዩኒቨርሲቲው ጋር ስምምነት የተፈራረሙ ተቋማትን ማወቅ ያለንን ሀብት ተጠቅመን ለሀገርና ለአካባቢያችን ተጨባጭ ውጤት ለማምጣት የሚጠበቅብንን እንድንሠራ ያዘጋጀናል ብለዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት