Print

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የፊታችን ዓርብ ሐምሌ 29/2014 ዓ/ም ከጧቱ 02፡30 – 05፡30 ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም ቅዳሜ 30/2014 ዓ/ም ከጧቱ 02፡30 – 05፡30 ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በማይንድ ሴት/Mind-Set/ ላይ ያተኮረ ፐብሊክ ሌክቸር በዋነው ግቢ መግቢያ በር አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ አዘጋጅቷል፡፡

የዓለም አቀፍ ወጣቶች ፌሎውሽፕ ኢትዮጵያ ሊቀመንበር እና የልቦና ውቅር ትምህርት ስፔሻሊስት (International Youth Fellowship Ethiopia Chairman and Mind-Set Education Specialist) የሆኑት ዶ/ር ቾ ሱንግዋ (Dr Cho Sunghwa) የሚያቀርቡ ይሆናል፡፡ ስለሆነም በተገለጸው መርሃ-ግብር መሠረት በመገኘት እንድትታደሙ የተጋበዛችሁ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያስታውቃል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት