Print

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብሮች አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ፈተና መስጠቱ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሠረት ከተወዳዳሪዎች መካከል በውጤታቸው መሠረት ወደ ዩኒቨርሲቲው እንዲገቡ የተመረጡ ዕጩዎች የቅበላና ምዝገባ ቀን በቅርብ ቀን ውስጥ የምንገልጽ መሆኑን እየሳወቅን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ የሚገቡ ነገሮችን በቅድሚያ ማሳወቅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-

1) የቅበላና ምዝገባ ጥሪ ሲተላለፍ የቅበላ ደብዳቤ (Admission letter) ለመውሰድ እና ምዝገባ ለመፈፀም ወደ ዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ተማሪዎች ቅበላና ምዝገባ ቡድን ቢሮ ቁጥር 210 እና 211 ስትመጡ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን በተላለፈው መመሪያ መሠረት በማስተርስ ዲግሪ ትምህርት ለመቀጠል ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ እንዲሁም በፒ.ኤች.ዲ. ትምህርት ለመቀጠል ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ ሕጋዊነትና ትክክለኛነት በባለሥልጣኑ የተረጋገጠ ስለመሆኑ ማስረጃ ይዘው መቅረብ እንዳለባቸው እና

2) ሁሉም በማስተርስ ዲግሪ ትምህርት ለመቀጠል ያመለከቱ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ ኦፍሻል ትራንስክሪፕት እንዲሁም ሁሉም በፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ ትምህርት ለመቀጠል ያመለከቱ አመልካቾች የሁለተኛ ዲግሪ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ወደ ዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት በኢሜይል  This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 21 አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በኩል ማስላክ እንዳለባቸው ከወዲሁ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት