Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ‹‹Biodiversity Conservation and Management›› ትምህርት ፕሮግራም የ3 ዲግሪ  ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ተመስገን ዲንጋሞ የፊታችን ሰኞ ጥቅምት 21/2015 ዓ/ም የመጨረሻ የምርምር ሥራቸውን የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች በተገኙበት በዓባያ ካምፓስ በፒ.ኤች.ዲ አዳራሽ ያቀርባሉ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ተመስገን ‹‹Land Cover Changes, Vegetation Ecology, and Carbon Stock Estimation in the Western Escarpment of Rift valley in the Gamo Zone, Southern Ethiopia›› በሚል ርዕስ የመመረቂያ ጥናት ያካሄዱ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት