Print

መ/ር ወንዱ ዳባ ከአባታቸው ከአቶ ዳባ ሞጆ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ደስታ አመኑ በቀድሞ ሰሜን ኦሞ ዞን ጋርዱላ አውራጃ በጊዶሌ ወረዳ ጥር 7/1965 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

መ/ር ወንዱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ክ/ሀገር በጊዶሌ ወረዳ ጊዶሌ መለስተኛ 1 ደረጃ ት/ቤት፣ እንዲሁም የ2 ደረጃ  ትምህርታቸውን በጊዶሌ 2 ደረጃ  ት/ቤት አጠናቀዋል፡፡

መ/ር ወንዱ ከአርባ ምንጭ መ/ራን ማሠልጠኛ ተቋም ሰኔ 1985 ዓ/ም በአንድ ዓመት ሥልጠና /TTI/ መ/ርነት፣ በሀዋሳ መ/ራን ትምህርት ኮሌጅ መስከረም 7/1997 ዓ/ም በቋንቋ ትምህርት ዲፕሎማ፣ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት 26/2003 ዓ/ም በእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሑፍ  የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን እንዲሁም የ2 ዲግሪያቸውን ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ“Teaching English as Foreign Language /TEFL/” ታኅሣሥ 6/2010 ዓ/ም አግኝተዋል፡፡  

መ/ር ወንዱ ከሐምሌ 1/1985-1989 ዓ/ም በሰሜን ኦሞ ዞን ቦረዳ ወረዳ በዞንጋ ዋጫ 1 ደረጃ ት/ ቤት፣ ከመስከረም 1990 - ነሐሴ 1991 ዓ/ም በኮዶ ጋምቤላ 1ደረጃ ት/ቤት፣ ከመሰከረም 1992 ዓ/ም - ጥር 21/1993 ዓ/ም በጋጋ ጎቾ 1ደረጃ ት/ቤት፣ ከ1993 - 1998 ዓ/ም በመኑካ 1 ደረጃ ት/ቤት፣ ከመስከረም 29/1999 ዓ/ም - 2002 ዓ/ም በቦረዳ ሙሉ 1 ደረጃ ት/ቤት፣ ከመስከረም 11/2003 ዓ/ም - ጥቅምት 8/2008 ዓ/ም በቦረዳ 2 ደረጃ ት/ቤት እና ከጥቅምት 9/2008 ዓ/ም እስከ ሕይወታቸው እሰካለፈበት ዕለት ድረስ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት በቋንቋ መምህርነት  ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡

መ/ር ወንዱ ባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ50 ዓመታቸው ጥቅምት 17/2015 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመ/ር ወንዱ ዳባ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት