Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በሂሳብ ት/ክፍል በ“Operation Research” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ ፀጋዬ ነገ ቅዳሜ ኅዳር 03/2015 ዓ.ም ከረፋዱ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በዓባያ ካምፓስ በፒ.ኤች.ዲ. አዳራሽ እንዲሁም በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ በማኔጅመንት ት/ክፍል በ“Marketing Management” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ዕጩ ዶ/ር ስንታየሁ አሰፋ  ረቡዕ ኅዳር 7/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመመረቂያ ፅሑፎቻቸውን በማቅረብ የሚያስገመግሙ ይሆናል፡፡ በመድረኩም የውጭና የውስጥ ገምጋሚዎችና አማካሪዎች ይገኙበታል፡፡

የዕጩ ዶ/ር ሀብታሙ ፀጋዬ የመመረቂያ ፅሑፍ “Application of Intuitionistic Fuzzy Optimization Technique in the Determination of Optimal Cropping Pattern” የሚል ሲሆን የዕጩ ዶ/ር ስንታየሁ አሰፋ ደግሞ “Drivers and Impediments of Export Performance: Evidence from Textile and Garment Enterprises in Ethiopia” የሚል ነው፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት