Print

በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ለፊዚክስ ትምህርት ክፍል ቤተ-ሙከራ በተገዙ ቁሳቁሶች አጠቃቀም ዙሪያ የአሠልጣኞች ሥልጠና ከጥቅምት 28 -ኅዳር 11/2015 ዓ/ም ለተከታታይ 15 ቀናት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ


የፊዚክስ ት/ክፍል ኃላፊ ረ/ፕ ወንድማገኝ አንጁሎ እንደገለጹት ትምህርት ክፍሉ ለመማር ማስተማር የሚሆኑ የቤተ-ሙከራ ግብዓቶችን እና የሰው ኃይልን በማጠናከር ላይ ነው፡፡ ኃላፊው  እንደ ሴንሰር ካሲ፣ ሞባይል ሴንሰር ካሲ ያሉ ቁሳቁሶች መገዛታቸው በተወሰነ መልኩ በአስትሮኖሚና ስፔስ፣ ስፔስ ፊዚክስ እና ኒውክለር ሳይንስ ቤተ-ሙከራዎችን  ለማደራጀት እና ወደ ምርምር  ለመግባት ያስችላል ብለዋል፡፡ ትምህርት ክፍሉ በሦስት ነገሮች ማለትም  በአስትሮኖሚና ስፔስ፣ በኒውክለር ፊዚክስና በማቴሪያል ሳይንስ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሠራ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል፡፡ የተገዙት ቁሳቁሶችም ለምርምርና መማር ማስተማር የሚሆኑ የአድቫንስ ላቦራቶሪ ግብዓቶች መሆናቸውን ረ/ፕ ወንድማገኝ አሳውቀዋል፡፡

አሠልጣኝና የአፍሮ ኬሚካል ኢንደስትሪ  የፊዚክስ ባለሙያ  ቤቴልሄም አሰፋ በበኩላቸው  ሥልጠናው እየተሰጠ የሚገኘው በሶፍትዌር አጠቃቀሞች ዙሪያ ነው ብለዋል:: ድርጅቱ  የራሱ የሆነ የተለየ ሶፍትዌር አለው ያሉት አሠልጣኟ ሥልጠናው በ“Data Recording”፣ በ‹‹Sensor CASSY-2”፣ በ“Sensor CASSY Lab”፣ በ“Softwere”፣ በ“Documente Center”፣ በ“LD DIDACTIC” እና በ“LaY Lab” ዕቃዎችና ማኑዋሎች እንዲሁም ሊፍሌቶችና ሞባይል ካሲ መጠቀም የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
እንደ አሠልጣኟ ሥልጠናው በተለይ ከፊዚክስ ጋር ተያይዞ በ“Classical Physics” “Mechanics” እና “Electronics”፣ በ“Modern Physics” “Quantum Physics” “Nuclear and Atomic Physics” እና “Wave and Optics” የተሰኙትን  ከሜካኒክስና  ቤተ-ሙከራ ጀምሮ እስከ አድቫንስ ፊዚክስ  ቁሳቁሶቹን  ተጠቅመው ንድፈ ሃሳብን ወደ ተግባር መቀየር የሚችሉበትን የአጠቃቀም አቅም ይፈጥራል፡፡

የአፍሮ ኬሚካል ኢንደስትሪ ድርጅት ቴክኒካል አሲስታንት አቶ ወንድማገኝ ደቻሳ እንደገለጹት ለዩኒቨርሲቲው የመጡት የላቦራቶሪ ቁሳቁሶች የመሬት “ማግኔቲክ ፊልድ”፣ “ኦብቲክስ”፣ “ሜካኒክስ”፣“ሂት አውቶሚክ” እና “ኒውክለር ፊዚክስ” 30 ቁሳቁሶችና ሌሎችም  በጥንድ ያሉ በመሆኑ በአጠቃላይ ከ60 በላይ ናቸው፡፡ ድርጅቱ በቤተ-ሙከራ ቁሳቁሶች አጠቃቀምና አሠራር ዙሪያ ሥልጠና መስጠትና በቀጣይም ክትትል የሚያደርግ መሆኑን አቶ ወንድማገኝ አሳውቀዋል፡፡
ሠልጣኝና የፊዚክስ ትምህርት ክፍል የቴክኒካል ቺፍ አሲስታንት መ/ር አድማሱ አበራ በሰጡት አስተያየት አዳዲስ የፊዚክስ ላቦራቶሪ ቁሳቁሶችን ለመጠቀም ዝግጅት ላይ መሆናቸውንና የመጡት ቁሳቁሶችም ከዚህ ቀደም ከምጠቀሟቸው ቁሳቁሶች በጣም ልዩነት ያለቸውና  ዘመናዊ ናቸው ብለዋል፡፡

በሥልጠናው “ሴንሰር ካሲ”፣ ሞባይል “ሴንሰር ካሲ”፣ “ሶፍትዌር”፣ “ዳታ ሪከርዲንግ”፣ “ሚልኪያን ኦይል ድሮፕሌት” እና  “ኤሌክትሮን”ን በጥልቀትና በተግባር ያየንበት እና ዘመኑ የደረሰበትን አልትራሳውንድ፣ ኤክስሬይ፣ የመሳሰሉትን በሳይንሱ ለማየት ተችሏል፡፡ ለአንድ ኤክሰፐርመንት የመጣው ዕቃ ለብዙ የተለያዩ ኤክስፐርመንቶች እንደሚያገለግል በመታየቱ ተማሪዎቻቸውን ለማስተማር ጉጉት እንዳሳደረባቸው ጠቁመው የተወሰኑ የጎደሉ  ዕቃዎች ቢኖሩም አሁን ትልቅ ችግር መቀረፉን መ/ር አድማሱ ተናግረዋል፡፡
                                                                                                                                                                                                                                  የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት