Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ምግባርና ፀ/ሙ/መከ/ዳይሬክቶሬት ቅዳሜ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም ጧት ከ2፡00 ሰዓት ጀምሮ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመጡበትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ በትምህርት ቆይታቸው ሊተገብሩ የሚገባቸውን የሥነ-ምግባር መርሆዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ዲሲፕሊን መመሪያን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና አዘጋጅቷል፡፡

ስለሆነም ሥልጠናው የሚመለከታችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በቴክኖሎጂ ትልቁ አዳራሽ በመገኘት ሥልጠናውን እንድትካፈሉ እናሳውቃለን፡፡

መልካም ተግባራት ከቃላት በላይ አስተማሪ ናቸው!

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥነ-ምግባርና ፀ/ሙ/መከ/ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት