Print

በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ“Computing and Software Engineering” ትምህርት ፕሮግራም ላለፉት 4 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል ሰኔ 02/2015 ዓ/ም የውስጥና የውጭ ገምጋሚዎች በተገኙበት የመመረቂያ ጽሑፉን አቅርቧል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ዕጩ ዶ/ር መሳይ ጥናቱን ‹‹Offline Handwritten Amharic Character Recognition Using Deep Learning›› በሚል ርእስ ያከናወነ ሲሆን የመመረቂያ ጽሑፉም አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላት በአማካሪ ቦርዱ ተቀባይነት አግኝቷል፡

ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል የመጀመሪያና የ2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በአርባ ምንጭ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪውን በኮምፒውተር ሳይንስ ከባሕር ዳር እና 2ኛ ዲግሪውን በኢንፎርሜሽን ሳይንስ ከጂማ ዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል፡፡

ዕጩ ዶ/ር መሳይ ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በቴክኒካል ረዳትነት፣ በመምህርነትና በተለያዩ ኃላፊነቶች ሲያገለግል ቆይቶ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል አግኝቶ በጀርመን ሀገር በዳድ ኢትዮ-ጀርመን ሀገር በቀል የፒ.ኤች.ዲ ስኮላርሽፕ/DAAD Ethio-German Home Grown Scholarship/ ድጋፍ አማካኝነት በጀርመን ሀገር በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሂልደሼይም/University of Hildesheim/ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተከታትሎ አጠናቋል፡፡

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉነህ ለማ በኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ምክንያቶች የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ቁጥር አለማደጉን ገልጸው ዕጩ ዶ/ር መሳይ አመርቂ ሥራ ሠርተው መመረቃቸው ለቀጣይ ተማሪዎች ምሳሌ የሚሆንና የሚያበረታታ ነው ብለዋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር ነቢዩ የማነ እንደገለጹት ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል በዩኒቨርሲቲው 25ኛ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፍ አቅራቢ ሲሆን ያገኘው ውጤትም ለሌሎች የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የማነቃቂያ አስተዋጽኦ ያለው ነው፡፡

በመርሃ ግብሩ የውስጥና የውጭ ገምጋሚዎች፣ የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር፣ የፋከልቲው መምህራንና የድኅረ ምረቃ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል የዶክትሬት ዲግሪው በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

በምርምር ሥራው ከአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ፕ/ር ዲፒ ሻርማ/Prof DP Sharma/ በዋና አማካሪነት እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሂልደሼይም/ University of Hildesheim/ ፕ/ር ዶ/ር ዶ/ር ላርስ ስችሚድ-ቲዬም /Prof. Dr. Dr. Lars Schmidt-Thieme/ እና ዶ/ር ኢ/ር አብዮት ሲናሞ/Dr Eng. Abiot Sinamo/ ከኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በራዳት አማካሪነት ተሳትፈዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት