Print

አቶ ማቴዎስ ገነሞ ከአባታቸው ከአቶ ገነሞ ዶክሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ማታፌ ጩቃሎ በቀድሞ በወላይታ ክፍለ ሀገር በአረካ ወረዳ አርፍጣ አጅማንቾ ቀበሌ ጥር 1/ 1956 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

አቶ ማቴዎስ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርፋጣ አጅማንቾ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት 1ኛ - 5ኛ ክፍል፣ በአርባ ምንጭ ኩልፎ መለስተኛ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ6ኛ - 8ኛ ክፍል እንዲሁም በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሠናዶ ትምህርት ቤት ከ9ኛ - 12ኛ ክፍል ያለውን የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ተከታትለዋል፡፡

አቶ ማቴዎስ ከአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሆቴልና ቱሪዝም መስክ የሆቴል ክቺን ኦፕሬሽን/Hotel Kitchen Operation/ ትምህርት ከ2006 ዓ/ም - መስከረም 1 /2008 ዓ/ም ተከታትለው የደረጃ II ምስክር ወረቀት አግኝተዋል፡፡

አቶ ማቴዎስ ከኅዳር 10/1979 ዓ/ም - ግንቦት 8/1985 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት በጠቅላላ አገልግሎት ሠራተኛ፣ ከግንቦት 09/1985 ዓ/ም - የካቲት 30/1991 ዓ/ም በተማሪዎች ካፍቴሪያ ሠራተኛ፣ ከመጋቢት 01/1991 ዓ/ም - ሰኔ 30/1997 ዓ/ም የቦይለር ኦፕሬተር ሠራተኛ፣ ከሐምሌ 01/1997 ዓ/ም - ሰኔ 30/2004 ዓ/ም ረዳት የተማሪዎች ምግብ ቤት ኃላፊ፣ ከሐምሌ 01/2004 ዓ/ም - ታኅሣሥ 30/2006 ዓ/ም በተማሪዎች አገ/ማዕ/ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች ምግብ ቤት ፈረቃ አስተባባሪ፣ ከጥር 01/2006 ዓ/ም - ሐምሌ 30/2009 ዓ/ም በጫሞ ካምፓስ የተማሪዎች የምግብ ቤት ፈረቃ አስተባባሪ፣ ከነሐሴ 01/2009 ዓ/ም - ጳጉሜ 05/2010 ዓ/ም በአምቴኢ የተማሪዎች ምግብ ቤት ፈረቃ አስተባባሪ እና ከመስከረም 01/2011 ዓ/ም  ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ሰኔ 05/2015 ዓ/ም ድረስ በዓባያ ካምፓስ የመስተንግዶ አገልግሎት ኃላፊ ሆነው በታታሪነት፣ በቅንነትና በታመኝነት አገልግለዋል፡፡

አቶ ማቴዎስ ባለትዳር፣ የአምስት ሴትና የሁለት ወንድ ልጆች አባት ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ59 ዓመታቸው ሰኔ 05/2015 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአቶ ማቴዎስ ገነሞ ኅልፈተ ሞት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቻቸው፣ ለሥራ ባልደረቦቻቸውና ለጓደኞቻቸው እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት