Print

ወ/ሮ ትዕግስት አበራ ከአባታቸው አቶ አበራ ከበደ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ምሳኤ ምትኩ በቀድሞ ጋሞ ጎፋ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ሚያዝያ 03/1970 ዓ/ም ተወለዱ፡፡ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ ከተማ ኃይሌ ደጋጋ 1ኛና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እና የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርባ ምንጭ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃና መሠናዶ ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት ከአርባ ምንጭ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ10+2 እና በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ-ክርስቲያን ደቡብ ምዕራብ ሲኖዶስ አርባ ምንጭ መካነ ኢየሱስ ቴክኒክ ኮሌጅ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በ10+3 በዲፕሎማ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ሰኔ 28/2006 ዓ/ም ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በማኔጅመንት የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት አበራ ከኅዳር 1997 - ታኅሣሥ 30/2000 ዓ/ም በማይክሮቴክ ኮምፒውተር ማሠልጠኛ ማዕከል በቢሮ ጸሐፊነት ያገለገሉ ሲሆን የካቲት 07/2000 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተቀጥረው እስከ መጋቢት 30/2002 ዓ/ም በኮንትራት የተማሪዎች ሪከርድ ሠራተኛ፣ ከሚያዝያ 01-30/2002 ዓ/ም በቋሚ ቅጥር የተማሪዎች ሪከርድ ሠራተኛ፣ ከግንቦት 01/2002 - ሰኔ 30/2004 ዓ/ም የቢሮ አስተዳደር፣ ከሐምሌ 01/2004 - ሰኔ 30/2005 ዓ/ም ኤክስኪዩቲቭ ሴክሬተሪ፣ ከሐምሌ 01/2005 - ታኅሣሥ 04/2006 ዓ/ም የሠርኩሌሽን ቡድን አስተባባሪ፣ ከጥር 05/2006 - ታኅሣሥ 30/2008 ዓ/ም የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ሠራተኛ፣ ከጥር 01/2008 - ነሐሴ 30/2010 ዓ/ም የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ሠራተኛ II እንዲሁም ከመስከረም 01/2011 ዓ/ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የዲጂታል ቤተ-መጻሕፍትና ኦቶሜሽን ባለሙያ IV በመሆን አገልግለዋል፡፡

ወ/ሮ ትዕግስት አበራ ባለትዳር ሲሆኑ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ45 ዓመታቸው ሰኔ 08/2015 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በወ/ሮ ትዕግስት አበራ ኅልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ ለሟች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች፣ ጓደኞችና የሥራ ባልደረቦች እንዲሁም ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ መጽናናትን ይመኛል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት