Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በሥጋ ቁጥጥርና አያያዝ ዙሪያ በተቋቋመ ፕሮጀክት አማካኝነት ‹‹Enhancing Slaughter House Service›› በሚል ርዕስ ከጋሞ ዞን ከተመረጡ የቄራ አገልግሎት ማዕከላት ለመጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ከሰኔ 21-23/2015 ዓ/ም ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ደግፌ አሰፋ እንደገለጹት የሰው ልጅ ከእንስሳት ተገቢውንና ጤንነቱ የተጠበቀ ጥቅም እንዲያገኝ የእንስሳቱን ጤና መጠበቅ እንዲሁም ከግዢ ጀምሮ እንስሳት ተጓጉዘው ወደ ቄራ አገልግሎት መስጫ እስኪደርሱና ለእርድ እስኪቀርቡ ድረስ ያለውን ሂደት ማሻሻልና ማዘመን ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

የኮሌጁ የማኅበረሰብ ጉድኝት አስተባባሪ አቶ ሰለሞን ይግረም በበኩላቸው ሥልጠናው በዘርፉ ባለሙያዎች በተደረገው የመስክ ምልከታ መሠረት የተዘጋጀ ሲሆን በዞኑ የተለዩትን የቄራ አገልግሎቶች ለመደገፍና የባለሙያዎችን አቅም በመገንባት ጥራቱን የጠበቀ የሥጋ አቅርቦት እንዲኖር ያግዛል ብለዋል፡፡

በሥልጠናው በኮሌጁ የእንስሳትና የኅብረተሰብ ጤና (Veterinary Public Health) መምህርና በጋሞ ዞን በተመረጡ የቄራ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት የአገልግሎት ማሻሻያ ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር እድገት ዓባይነህ ‹‹The Overall Scenarios of Abattoir Practice Status of Selected Slaughter Houses in Gamo zone, Provision of Personal Protective Equipment(PPE) for Selected three Project Area Abattoirs›› እና ‹‹Abattoir Service Issues, Good Manufacturing Practice and Hazard Analysis Critical Control Point (HACCP) System››፣ በሌላኛው የት/ክፍሉ መምህር ዶ/ር ምናለ ጌታቸው ‹‹General Postmortem (PM) Lesion in Abattoir and their Disposition›› እንዲሁም በአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሰው ሀብት ልማት ስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት ባለሙያ ዶ/ር አበባው አስናቀ ‹‹Abattoir Standards and Regulatory Issues in Ethiopia›› በሚሉ ርእሶች ጽሑፎች ቀርበዋል፡፡

ዶ/ር እድገት ፕሮጀክቱ ምርምርን መሠረት በማድረግ በተገኙ ውጤቶች ላይ በመመርኮዝ በዞኑ በተመረጡ ማዕከላት የቄራ  አገልግሎቶችን ለማሻሻልና ለማዘመን የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ እንደሚሠራና በተለይ ከእንስሳት ወደ ሰውና ከሰው ወደ እንስሳት የሚተላለፉ በሽታዎችን መከላከልን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን እንደሚያከናውን ተናግረዋል፡፡

ከአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የቄራ አገልግሎት ባለሙያ ዶ/ር ገነት ታደሰ ‹‹Common Postmortem (PM) Lesion Encountered in Arba Minch›› በሚል ርእስ በሥራ ቆይታቸው ካገኙት ተሞክሮ በመነሳት አገልግሎቱ በከተማውና በአካባቢው ለብዙኃኑ በምን መልኩ ተደራሽ መሆን እንዳለበት፣ በየጊዜው ሊያጋጥሙ የሚችሉ ጉዳቶችን መከላከል፣ እንዲሁም በእርድ ወቅት መደረግ በሚገባቸው ጥንቃቄዎች ዙሪያ ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡

በሥልጠናው ማጠቃለያ የአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የቄራ አገልግሎት መስጫ ማዕከል የደረሰበትን ደረጃ በተለይ ከቆዳ አያያዝና ከእንስሳት እርድ ንጽሕና ጋር በተያያዘ በማዕከሉ በምን ሁኔታ በጥንቃቄ እየተተገበረ እንደሚገኝ ተሳታፊዎች ተዘዋውረው በመጎብኘት ለአገልግሎቱ ዘላቂነት የሚረዱ ሐሳቦችን ሰጥተዋል፡፡ በዳሰሳ ጥናት ተለይተው ለተመረጡ አርባ ምንጭ፣ ጨንቻና ሰላምበር  የቄራ አገልግሎት ማዕከላትም 60 ሺህ ብር የሚያወጡ የቱታ፣ ጋዋንና ቦቲ ጫማ ድጋፍ ተበርክቷል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት