Print

‹‹Brighter Generation›› የተሰኘ ድርጅት ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹STEM›› ማዕከል ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተወጣጡ የተሻለ የመግባባት ችሎታና የትምህርት ውጤት ያላቸው የ9ኛና 10ኛ ክፍል ተማሪዎች ለ10 ሳምንታት የሚቆይ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተግባቦትና የአመራር ክሂሎት የበይነ-መረብ ሥልጠና ለመስጠት ሰኔ 17/2015 ዓ/ም የማስጀመሪያ መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የማዕከሉ አስተባባሪ ዶ/ር ቢንያም ወንዳለ እንደገለጹት ሥልጠናው በሳምንት ሁለት ሰዓት አውሮፓ፣ አሜሪካና ካናዳ ባሉ አሠልጣኞች በበይነ-መረብ የሚሰጥ ሲሆን በትምህርት ውጤታቸው ከፍ ያሉና የተሻለ የመግባባት ችሎታ ያላቸው 20 ተማሪዎች ለሥልጠናው ተመርጠዋል፡፡

የእንግሊዝኛ ቋንቋ ት/ክፍል መምህርና የሥልጠናው አስተባባሪ ዶ/ር ጋሻው ተፈራ በበኩላቸው ሥልጠናው በመላው ሀገሪቱ በ35 ‹‹STEM›› ማዕከላት በተመሳሳይ ሰዓት የሚሰጥና ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ከሚያገኙት ዕውቀት በተጨማሪ የወደ ፊት ማንነታቸውን እንዲቀርጹ የሚያስችላቸው የክረምት ትምህርት መርሃ ግብር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ‹‹STEM›› ማዕከል አስተባባሪና ሠራተኞች፣ ተማሪዎችና የተማሪዎች ወላጆች ተገኝተዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት