Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ማጠቃለያ ውጤት በመረጃ መረብ (Online) የተለቀቀ ስለሆነ ከታች የቀረበውን ሊንክ በመጫን (ወይም ሊንኩን በዌብ ፔጅ ላይ ኮፒ-ፔስት በማድረግ)፣ መለያ ቁጥር (ID Number) በማስገባት፣ Search እና View Result በመጫን ማየት የሚትችሉ መሆኑን እየገለጸ በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተማሪ ካለ ከሰኞ እስከ ረቡዕ (ከነሐሴ 1 እስከ 3/ 2015 ዓ.ም) ባለው ጊዜ ውስጥ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቢሮ (የአምዩ አስተዳደር ሕንጻ 2ኛ ፎቅ) ማመልከት የሚችል/ትችል መሆኑን ያሳውቃል፡፡

https://survey.amu.edu.et/remedial/

ማሳሰቢያ፡- ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚቀርብ የቅሬታ ማመልከቻ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት