Print

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በአሜሪካ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ስኮላርሽፕ ዕድል መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ከኤምባሲው የመጡ ተወካዮች ለዩኒቨርሲቲው መምህራን ነገ ረቡዕ ነሐሴ 10/2015 ዓ/ም ከጧቱ 04፡00 ሰዓት በዋናው ግቢ መግቢያ በር አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ ገለጻ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ የዩኒቨርሲቲው መምህራን በዘርፉ ባሏችሁ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እንድታገኙ ዩኒቨርሲቲው መድረክ ያመቻቸ መሆኑን እየገለጸ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተገኝታችሁ ዕድሉን እንድትጠቀሙ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

በተመሳሳይም ከአካባቢው ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች በርዕሳነ መምህራን አማካኝነት የተመረጡ ተማሪዎች በአሜሪካ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ስኮላርሽፕ ዕድል በሚያገኙበት ሁኔታ በተመሳሳይ አዳራሽ ነገ ከሰዓት ከቀኑ 08፡00 ሰዓት ጀምሮ ገለጻው የሚሰጥ በመሆኑ እንድትሳተፉ የተገለጸላችሁ የአርባ ምንጭ፣ የዓባያ፣ የሮኆቦት፣ የልማትና የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮሚዩኒቲ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቀደም ብላችሁ በመገኘት ፕሮግራሙን እንድትሳተፉ ዩኒቨርሲቲው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

 

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

 የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት