Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የግራንትና የትብብር ፕሮጀክቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ከውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሃይድሮሎጂና ሜትዎሮሎጂ ፋካልቲ ጋር በመተባበር ለፋካልቲው መምህራንና ለ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ከመስከረም 30 - ጥቅምት 01/2015 ዓ.ም ድረስ ለሁለት ቀናት የቆየ ሥልጠና ‹‹Satellite and Remote Sensing Applications›› በሚል ርዕስ ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የግራንትና የትብብር ፕሮጀክቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ቶማስ ቶሮራ የሳታላይትና ሪሞት ሴንሲንግ ቴክኖሎጂ ስለዝናብና ሙቀት መጠን ለመገመት የሚጠቅም ሲሆን ሥልጠናው በዘርፉ የሚያስተምሩ መምህራን ምርምር እንዲሠሩና ለተማሪዎች በምርምር የተደገፈ ትምህርት እንዲሰጡ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡  

የሃይድሮሎጂና ሜትዎሮሎጂ ፋካልቲ ዲን ዶ/ር ታደሰ ቱጁባ ሥልጠናው አሜርካን ሀገር ከሚገኘው ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተሰጠ ሲሆን ለምርምር ሥራ የአየር ንብረት መረጃ አጠቃቀም፣ መተንተን፣ ምንጮችን ማመላከት የሥልጠናው ትኩረቶች መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ሥልጠናው መምህራኑም ሆኑ 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች ለሚያከናውኗቸው የምርምር ሥራዎች በእጅጉ የሚያግዝ እንደሆነ ዲኑ ጠቁመዋል፡፡

በአሜርካ በሚገኘው ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ የምርምር ኢንስቲትዩት ተመራማሪ፣ ሳይንቲስትና አሠልጣኝ ዶ/ር ቱፋ ድንቁ ‹‹Satellite and Remote Sensing Applications›› በሚል ርዕስ የተሰጠው ሥልጠና ዋነኛ ዓለማው በዘርፉ የሚያስተምሩ መምህራን ክሂሎት ከማሳደግ ባለፈ ተማራማሪዎችና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የሳታላይት መረጃን እንዴት ማግኘት፣ መተንተንና ለምርምር ሥራቸው መጠቀም እንዲችሉ ማስቻል ነው ብለዋል፡፡

ከሠልጣኞች መካከል መ/ር ግዛቸው ካሳ በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው በዘርፉ ላይ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖረን አድርጓል ብለዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት