Print

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ማኅበራዊ ሳይንስና ሥነ ሰብ ኮሌጅ ‹‹Geography and Environmental Studies›› ት/ክፍል በ‹‹Environment and Natural Resource Management›› የትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር ገነሻ ማዳ የመመረቂያ ጽሑፍ ኅዳር 3/2016 ዓ/ም የውጪና የውስጥ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ የመመረቂያ ጽሑፉ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላቱ በአማካሪ ቦርዱ ጸድቋል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

ዕጩ ዶ/ር ገነሻ ማዳ የመጀመሪያ ዲግሪውን በ‹‹Geography and Environmental Education›› እና ሁለተኛ ዲግሪውን በ‹‹Land Use Management›› ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል፡፡ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን በ‹‹Natural Resource and Environmental Management›› በ2010 ዓ/ም የጀመረው ዕጩ ዶ/ር ገነሻ የመመረቂያ ጥናታዊ ጽሑፉን ‹‹Ecosystem Services and Degradation of Plantation Forest Analysis in the Upper Hare-Baso River Catchment of Gamo Highlands; Southwestern Ethiopia›› በሚል ርእስ አከናውኗል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ዶ/ር ውባለም ታደሰ ከ‹Lead Researchers Ethiopian Forestry Development›› እና ዶ/ር መኮንን አድነው ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በውጪ ገምጋሚነት እንዲሁም ዶ/ር ሠረቀብርሃን ታከለ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ  በውስጥ ገምጋሚነት ተሳትፈዋል፡፡

ዕጩ ዶ/ር  ገነሻ ማዳ የዶክትሬት ዲግሪውን በዩኒቨርሲቲው ሴኔት ከጸደቀ በኋላ የሚያገኝ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት