Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ት/ቤት ተማሪ የሆኑት መቅደላይት ፈቃደ፣ ሰላማዊት ይብዛው እና ሜላት ገ/መድኅን ከግንቦት 29-30/2023 በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ በተካሄደው አምሳለ ፍርድ ቤት ውድድር ከሐሮማያ፣ ጅማ፣ ድሬዳዋ፣ ባሕር ዳር እና ሰላሌ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ጋር በመወዳደር በሀገር አቀፍ ደረጃ አሸናፊ ሆነው ለአህጉራዊ ውድድር ኢትዮጵያን ወክለው እንዲገኙ መመረጣቸው ይታወሳል፡፡ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በዚህ መሠረት ኅዳር 26/2016 ዓ/ም በታንዛኒያ አሩሻ ከተማ በተካሄደው አህጉራዊ ውድድር ሀገራችን ኢትዮጵያን ወክለው ተወዳድረው 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነው ተመልሰዋል፡፡ ባገኙት ውጤት የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ከፍተኛ ደስታ የተሰማው ሲሆን በማዕከልና በካምፓስ ደረጃ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጓል፡፡ በቀጣይም የተማሪዎቹን አርአያነት በሚመጥን ደረጃ ተቋማዊ አቀባበል የሚደረግና ዕውቅና የሚሰጥ ይሆናል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት