Print

በ2016 የትምህርት ዘመን የድኅረ ምረቃ ትምህርት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ለመማር አመልክታችሁ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ቅበላ ፈተና (National Graduate Admission Test – NGAT) ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያመጣችሁና የተመዘገባችሁ አዲስ አመልካች ተማሪዎች ፡-

@ የዩኒቨርሲቲ አቀፍ መግቢያ ፈተና የሚሰጠው  ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ለመማር ባመለከታችሁበት ኢንስቲትዩት ወይም  ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት፤

@ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን ብሔራዊ የድኅረ ምረቃ ቅበላ ፈተና (National Graduate Admission Test – NGAT) ወስዳችሁ በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገባችሁ እና አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የሚትፈልጉ ኅዳር 24 እና 25 ቀን 2016 ዓ.ም ሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 210 እና 211 ቀርባችሁ መመዝገብና ኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን ፈተና በመቀበል መማር የሚትቸሉ፤

@ ከፈተና በኋላ የሬጅስትራር ምዝገባ የሚካሄደው ኅዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም እና

@ መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት ታኅሣሥ 01 ቀን 2016 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፡ -
@ የማስተርስ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም የፒ.ኤች.ዲ ዲግሪ አመልካቾች የመጀመሪያና የሁለተኛ ዲግሪ ኦፍሻል ትራንስክሪፕት በፖስታ ሳጥን ቁጥር 21 ወይም በተቋማዊ ኢሜይል አድራሻዎች፡- This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ወይም This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. በኩል በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ማስላክ ይጠበቅባቸዋል፡፡

@ የማታ እና የሳምንት መጨረሻ ፕሮግራም አመልካቾች በቂ ተማሪ ባልተገኘባቸው ፕሮግራሞች ከመደበኛ ተማሪዎች ጋር መማር የሚትችሉበት ሁኔታ ማመቻቸት ይጠበቅባቸዋል፡፡


የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!

ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-

ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት