Print

የሲ.ኤስ.አይ.ቲ (CSIT) እና ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ት/ት ክፍል ክበብ በ2010 ዓ/ም በት/ክፍሉ አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁና የክበቡን ዓላማ የማስተዋወቅ ፕሮግራም ጥቅምት 28/2010 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

ክበቡ ሁሉንም የትምህርት ክፍሉን አባላት ባሳተፈ መልኩ የማጠናከሪያ ትምህርት ድጋፍ በማድረግና ተማሪዎች በጋራ ጉዳዮች ላይ እንዲመክሩ በማመቻቸት ክህሎታቸውን እንዲያሻሽሉና በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማገዝ የተቋቋመ መሆኑን የክበቡ ፕሬዝደንት ተማሪ ፈቃዱ ሙለታ ገልጿል፡፡ ድጋፉ ተማሪዎች ትርፍ ጊዜያቸውን ባልተገባ ቦታና ተግባር እንዳያሳልፉ በማድረግ በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ስኬታማ እንደሚያደርጋቸውም ተናግሯል፡፡

ተማሪዎች ለሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ትኩረት ሰጥተው በአግባቡ በመከታተልና ጠንክረው በመሥራት ውጤታማ ከመሆን ጎን ለጎን በመሰል ክበቦች በመሳተፍ ድጋፍ ማግኘትና ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባቸው የኮምፒዩተር ሣይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ት/ክፍል ኃላፊ አቶ ሲሣይ ቱምሳ አስገንዝበዋል፡፡

አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሥነ-ልቦና ጠንካራ እንዲሆኑ የሚቀሰቅሱ ተሞክሮዎች በትምህርት ክፍሉ መምህራንና ነባር ተማሪዎች የቀረቡ ሲሆን ሌሎች አዝናኝ ዝግጅቶችም ተካሂደዋል፡፡ የትምህርት ክፍሉ መምህራን፣ ተማሪዎችና ሌሎች እንግዶች በፕሮግራሙ ተሳትፈዋል፡፡