የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ትኩረት የሚሹ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ምርምርና ሥልጠና ማዕከል ከደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በጋሞ ዞን ለሚገኙ ነርሶች፣ ጤና መኮንኖች፣ ሐኪሞችና የላቦራቶሪ ባለሙያዎች በቁንጭር (Cutaneous Leishmaniasis)ና ሌሎች የቆዳ በሽታዎች ዙሪያ ከነሐሴ 24/2015 ዓ/ም ጀምሮ ለአምስት ቀናት የሚቆይ ሥልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በ2012 እና 2013 የትምህርት ዘመን ባጋጠመን የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽን ምክንያት መደበኛ የትምህርት ካላንደር መዛባቱ ይታወቃል፡፡ በወረርሽኙ ምክንያት የተከሰተውን የትምህርት ጊዜ ብክነት በማስተካከል ላይ የምንገኝ በመሆኑ የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2013 ባች (3 ዓመት ቅድመ ምረቃ) ተማሪዎች ቅበላ፣ ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀመርበት ቀን በልዩ ሁኔታ በጊዜ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከ “SNV-Rayee” ማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚገኙ ወጣት ሥራ ፈጣሪዎች የቢዝነስ ሃሳብ ውድድር ያዘጋጀ በመሆኑ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች በውድድሩ ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡

Arba Minch University is interested to recruit academic staffs for Sawla Campus in the following position and fields.

Position: - Assistant Lecturer (BA), Lecturer & Above

Qualification: - M.Sc./MA/MD/LLM/Ass. Prof., PhD & Above

Requirement: - CGPA≥3.50 for Postgraduate studies, Research Result: Very Good and above. Click here to see more Photos. 

ዕጩ ዶ/ር ማቲዎስ አግዜ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በባዮሎጂ ት/ክፍል በ ̋Biodiversity Conservation and Management” ትምህርት ፕሮግራም የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ ዕጩ ዶ/ር ማቲዎስ የ3ኛ ዲግሪ መመረቂያ ጽሑፉን የውስጥና የውጪ ገምጋሚዎች እንዲሁም አማካሪዎች በተገኙበት በዓባያ ካምፓስ አዲሱ የአስተዳደር ሕንጻ አዳራሽ ነሐሴ 29/2015 ዓ/ም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ የሚያቀርብ ይሆናል፡፡