አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ ዕቅዱን በዩኒቨርሲቲው ካውንስል ነሐሴ 5/2015 ዓ/ም አስገምግሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2015 በጀት ዓመት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ነሐሴ 5/2015 ዓ/ም ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል ቀርቦ ተገምግሟል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በአሜሪካ የድኅረ ምረቃ ትምህርት ስኮላርሽፕ ዕድል መጠቀም በሚቻልበት ሁኔታ ከኤምባሲው የመጡ ተወካዮች ለዩኒቨርሲቲው መምህራን ነገ ረቡዕ ነሐሴ 10/2015 ዓ/ም ከጧቱ 04፡00 ሰዓት በዋናው ግቢ መግቢያ በር አካባቢ በሚገኘው አዳራሽ ገለጻ የሚደረግ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ የዩኒቨርሲቲው መምህራን በዘርፉ ባሏችሁ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እንድታገኙ ዩኒቨርሲቲው መድረክ ያመቻቸ መሆኑን እየገለጸ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተገኝታችሁ ዕድሉን እንድትጠቀሙ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛው መርሃ-ግብር ለተመረቁ ተማሪዎች ወንድ 3.5 እና ከዚያ በላይ፣ ሴት 3.25 እና ከዚያ በላይ ውጤት ላስመዘገቡ በ2016 የትምህርት ዘመን ነፃ የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል 18 ተማሪዎች አወዳደሮ ለመስጠት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ የ2015 ትምህርት ዘመን ተመራቂ ተማሪዎች ከነሐሴ 02 - 20/2015 ዓ/ም ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት የተማሪዎች ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210 እና 211 እየቀረባችው እንድትመዘገቡ እየገለጽን፡-

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2015 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial) ማጠቃለያ ውጤት በመረጃ መረብ (Online) የተለቀቀ ስለሆነ ከታች የቀረበውን ሊንክ በመጫን (ወይም ሊንኩን በዌብ ፔጅ ላይ ኮፒ-ፔስት በማድረግ)፣ መለያ ቁጥር (ID Number) በማስገባት፣ Search እና View Result በመጫን ማየት የሚትችሉ መሆኑን እየገለጸ በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያለው ተማሪ ካለ ከሰኞ እስከ ረቡዕ (ከነሐሴ 1 እስከ 3/ 2015 ዓ.ም) ባለው ጊዜ ውስጥ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቢሮ (የአምዩ አስተዳደር ሕንጻ 2ኛ ፎቅ) ማመልከት የሚችል/ትችል መሆኑን ያሳውቃል፡፡