አቶ ማቴዎስ ገነሞ ከአባታቸው ከአቶ ገነሞ ዶክሌ እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ማታፌ ጩቃሎ በቀድሞ በወላይታ ክፍለ ሀገር በአረካ ወረዳ አርፍጣ አጅማንቾ ቀበሌ ጥር 1/ 1956 ዓ/ም ተወለዱ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከኢትዮጵያ የሥራ ፈጠራ ኢንስቲትዩት፣ ከሲሳይ ፕሮሞሽን ኢቨንት አዘጋጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝየም እና ከጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ጋር ያደረጉትን የተግባር ተኮር ልምድ ልውውጥ ሪፖርት ሰኔ 3/2015 ዓ/ም አቅርበዋል፡፡ በዕለቱም በዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ አጋርነት ትስስር በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡  ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የተደረገው የተግባር ተኮር ልምድ ልውውጥም ‹‹Assessment of Entrepreneurship and Business Development Practices of Entrepreneurship Development Institute (EDI)››፣ ‹‹Exchanging Knowledge in the Pre, on and Post Event Phases & Networking with Industry in Sisay Aderisse Promotion & Event Organizer Cooperative››፣ ‹‹Establishing Strategic Partnership and Experience Sharing with Hospitality Organization: Training Exposure at Jupiter International Hotel›› እና “Practices, Challenges and Gaps Between Theory and Practice in Museum Management: An Externship on the National Museum of Ethiopia›› ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝደንት እና የፕሬዝደንት ተወካይ ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ እንደገለጹት የኢንደስትሪ ትስስር መፈጠሩ ወደ ማኅበረሰቡ መውረድ የሚችሉ ምርምሮችን ለመሥራት እና ተግባር ተኮር ትምህርት በመስጠት ገበያው የሚፈልገውን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ ለማፍራት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡ ም/ፕሬዝደንቱ አክለውም ትምህርት በየወቅቱ ራስን ማብቃት የሚፈልግ በመሆኑ በቀጣይ ተቋሙ ለሚያመራው  የራስ ገዝ ጉዞ ከከፍተኛ አመራር ጀምሮ ያሉ የተቋሙ ሠራተኞች የሥራ ፈጠራ ልምድ እንዲያካብቱ የተሻለ የተግባር ተሞክሮ ባላቸው መምህራን ታቅዶ ሊሠራበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ ኮሌጁም በዚህ ረገድ እያካሄደ ያለው ተግባር የሚበረታታ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ  ዲን ዶ/ር መስፍን መንዛ በበኩላቸው መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ መከናወኑን አስታውሰው  በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና በኢንዱስትሪዎች መካካል ያለው ግንኙነት የጠበቀ ባለመሆኑ ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ አመላክተዋል፡፡ በመሆኑም የሁለቱ ወገን ስምምነት ዋና ዓላማ  ያላቸውንና በቀጣይ የሚኖራቸውን የሰው ኃይል አሠራር፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር በማድረግ የተግባር ልምድና በጀት በማስተባበር የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ውጤታማ በሆነ መልኩ በጋራ ለመወጣት የሚያስችል የማስፈጸም አቅም መፍጠር  እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም በጥናትና ምርምር ላይ በመመርኮዝ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ብሎም ሀገሪቷን ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ዲኑ ገልጸዋል፡፡

የሥራ ላይ ልምድ ልውውጥ ሪፖርት ያቀረቡ መምህራን በንድፈ ሃሳብ የሚያስተምሩትን ትምህርት በተግባር መመልከትና  የራሳቸውን የክሂሎት ክፍተት መሙላት የቻሉበት፣ በመምህራኑ ተለይተው በቀረቡ የኢንደስትሪው ተጨባጭ ችግሮች ዙሪያ  በቀጣይ የጋራ የሆነ ጥናት በማካሄድ ችግሮች እንዲፈቱ እንዲሁም ለሥርዓተ-ትምህርት ክለሳ ገንቢ የሆነ አስተያየት የተሰበሰበበትና ፍሬያማ ውይይት የተደረገበት እንደነበር ዶ/ር መስፍን ተናግረዋል፡፡   

የኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖለጂ ሽግግር ሥራ ከተቋሙ ተልዕኮ አንዱ ነው ያሉት የዩኒቨርሲቲው ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖለጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ቶሌራ ሴዳ ዩኒቨርሲቲውን ከሌሎች ተቋማት ጋር በማስተሳሰር በቴክኖሎጂ የሚፈጠሩ ሃሳቦችን ወደ እንደስትሪው እንዲሄዱ  የማድረግ ሥራ እንደሚሠራ ገልጸው የተግባር ልምዳቸውን ያቀረቡት መምህራን በንድፈ ሃሳብ ያላቸውን ዕውቀት በተግባር የማስደገፍ ሥራ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ ዶ/ር ቶሌራ አክለውም በቀጣይ የኢንደስትሪ ችግሮች ላይ በጋራ ምርምሮችን በመሥራት የኢንደስትሪውን ችግር በዘላቂነት መፍታትና እንደ ሀገር ሁሉም ተቋማትና ማኅበረሰብ በጋራ በመሥራት ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ የተፈራረሙ አካላትም በቀጣይ በሚኖሩ መርሃ ግብሮች አባል በመሆን እንዲሳተፉና በውል ስምምነቱ መሠረትም ወደ ሥራ እንዲገቡ አሳስበዋል፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የቀረቡ ሪፖርቶች የኢንደስትሪ ተቋማትን ጥንካሬና ድክመቶችን ያመላከተና መምህራኑ የተግባር ሥራዎችን በተገቢው የተማሩበት በመሆኑ የሚበረታታ ነው፡፡ የትብብር ሥራዎች ተጠናክረው በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ ተሞክሮዎች ተቀምረው መምህራን ልምድ እንዲያካብቱ፣ የትምህርት ሥርዓቱ እንዲሻሻል ማድረግና ተግባር ተኮር እንዲሆን መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡ በቀጣይ በሚኖሩ የጋራ የሥራ ተግባራት ጠንክረው በመሥራት የተሻሉ ተማሪዎችን ለማፍራትና  የሀገሪቱን ዕድገት ለማፋጠን ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

በፕሮግራሙ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት፣ የዩኒቨርሲቲው ኢንደስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን፣ የኢትዮጵያ የሥራ ፈጠራ ኢንስቲትዩት ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የሲሳይ ፕሮሞሽን ኢቨንት አዘጋጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት ሥራ አስኪያጅ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዝየም ዳይሬክተር፣ በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኪሊንቶ ኢንደስትሪያል ፓርክ ሲኒየር ኢንቫይሮሜንታሊስት ባለሙያ፣ የኮሌጁ መምህራንና ሌሎች  ተጋባዥ ባለድርሻ አካላት ታድመዋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
የብሩህ ተስፋ ማዕከል!
ለተጨማሪ መረጃ በድረ-ገጽና በማኅበራዊ ትስስር ገጾቻችን ይከተሉን፡-
ድረ-ገጽ - https://www.amu.edu.et/
ቴሌግራም - https://t.me/arbaminch_university
ፌስቡክ - https://www.facebook.com/ArbaMinchUniversityCCD/
ዩቲዩብ - https://www.youtube.com/channel/UCOO_nclhMo8M3r74OyPBlVA
የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጃፓይጎ ‹‹Jhpiego›› ከተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር የሴት መምህራን ፎረም/Women Academic Forum/ ለመመሥረት ሰኔ 02/2015 ዓ/ም ውይይት አካሂዷል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ“Computing and Software Engineering” ትምህርት ፕሮግራም ላለፉት 4 ዓመታት የ3ኛ ዲግሪ ትምህርቱን ሲከታተል የቆየው ዕጩ ዶ/ር መሳይ ሳሙኤል ሰኔ 02/2015 ዓ/ም የውስጥና የውጭ ገምጋሚዎች በተገኙበት የመመረቂያ ጽሑፉን አቅርቧል፡፡ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ