የአርባ ምንጭ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከደቡብ ክልል የመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲና ከደቡብ ክልል ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ድርጅት ጋር በመተባበር በመሎ ኮዛ ወረዳ ጨልቆ ወንዝና በቡርጂ ወረዳ ሰገን ወንዝ ላይ ለሚያሠራቸው የግድብና መስኖ ፕሮጀክቶች የጥናትና ዲዛይን ሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ነሐሴ 2/2014 ዓ/ም ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች አቅርቧል፡፡ ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት  መጨረሻ  መርሃ  ግብሮ  መስፈርቱን  የሚያሟሉ  አዲስ  አመልካቾችን ከዚህ  በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡ የፕሮግራሞችን ዝርዝር ለማየት እዚህ ይጫኑ

በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ እና በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ትብብር በግንባታ፣ በምክር አገልግሎት ግዥ፣ በውል አስተዳደርና ንብረት አያያዝ ዙሪያ ከነሐሴ 4-7/2014 ዓ/ም የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናና የተሞክሮ ልውውጥ መድረክ ተዘጋጅቷል፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ወልደአብ ደምሴ የሥልጠናው ዓላማ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማጋራትና ግንዛቤ በማስጨበጥ የግዥ አሠራሮች እንዲሻሻሉ እንዲሁም ባለሙያዎቹ የአመለካከት ለውጥ አምጥተው የራሳቸውን አሻራ ማሳረፍ እንዲችሉ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የግዥ ሥራ ጊዜ የማይሰጥና ውስብስብ በመሆኑ የሚሻሻሉ አዋጆችና የመመሪያ ለውጦችን በማየት ፈጻሚዎች በመተባበር እና ሕግና ሥርዓቱን ተከትሎ በመሥራት ኃላፊነታቸውን መወጣትና ራሳቸውን ማሻሻል እንደሚገባቸው ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ STEM ማዕከል ከዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ ጉድኝትና ከተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬቶች እንዲሁም ከ STEMpower መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር ከጋሞ፣ ጎፋና ኮንሶ ዞኖች እና ከደራሼ፣ ባስኬቶ፣ ቡርጂና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ለተወጣጡ 291 ከ7-12 ክፍል ተማሪዎች በኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ሒሣብ፣ ኤሌክትሮኒክስና ICT ትምህርቶች ከሐምሌ 15 - ነሐሴ 30/2014 ዓ/ም የሚቆይ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ከ15 ዓመት በታች በሁለቱም ፆታዎች የፓይለት ፕሮጀክት ምዘና ውድድር ከሐምሌ 17-ነሐሴ 1/2014 ዓ/ም ለመጀመሪያ ጊዜ በአርባ ምንጭ ከተማ አካሂዷል፡፡