- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የማኅበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለባልታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ማስተማር ሥራ የሚውሉ የባዮሎጂ፣ የኬሚስትሪና የፊዚክስ ቤተ-ሙከራ ኬሚካሎችና ቁሳቁሶችን ሚያዝያ 8/2014 ዓ/ም ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉ በገንዘብ ሲተመን 130,000 (አንድ መቶ ሠላሳ ሺህ) ብር የሚያወጣ መሆኑ ተገልጿል፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለባልታ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የቤተ-ሙከራ ኬሚካሎችና ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ
- Details
የአርባ ምንጭ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምርምርና ማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የዩኒቨርሲቲው የቀድሞ መምህር፣ ታዋቂ የፈጠራ ባለቤትና በIBM ካምፓኒ ውስጥ ተመራማሪ ከሆኑት ቺፍ አርክቴክት ዶ/ር ኮሚ ወ/ማርያም ጋር አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስን በዘላቂ የምግብ ዋስትናና ግብርናን በማዘመን ዘዴ በመጠቀም ላይ ሚያዝያ 7/2014 ዓ/ም ኦንላይን ሴሚናር አካሂዷል፡፡
Read more: አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስን በዘላቂ የምግብ ዋስትናና ግብርናን በማዘመን ዘዴ በመጠቀም ላይ ሴሚናር ተካሄደ
- Details
በአዲሱ የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ምርጫ መመሪያ መሠረት በ2012 ዓ.ም የተመረጠው የተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ ሁለት ዓመት የሥራ ዘመን መጠናቀቁን ተከትሎ በአዲስ አባላት ለመተካት ከታኅሣሥ 8/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ የነበረው የዋና ሥራ አስፈፃሚ ምርጫ ሂደት ሚያዝያ 02/2014 ዓ.ም ተጠናቋል፡፡ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኅብረት ፓርላማ የዋና ሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ አካሄደ
- Details
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ፎረም አባላትና የ2014 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎች ‹‹በፍቅር በመደመር ሰላማችንን እንጠብቅ›› እና ‹‹100 ቀናችንን በጽዳት ዘመቻና ችግኞችን ውሃ በማጠጣት እናሳልፍ›› በሚሉ መሪ ቃሎች በዋናው ግቢ የጽዳት ዘመቻና ችግኝ ውሃ የማጠጣት መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡
Read more: የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሰላም ፎረም አባላትና የ2014 ዓ/ም ተማራቂ ተማሪዎች የግቢ ጽዳትና ችግኝ የማጠጣት መርሃ ግብር አካሄዱ