- Details
አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከአርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በአግሮፕሮሰሲንግ ዘርፍ ለተሰማሩ አነስተኛና መካከለኛ ኢንደስትሪ አንቀሳቃሾች በምግብ ደኅንነት አስተዳደር ሥርዓት (FSMS:ISO 22000፡2018) ዙሪያ ታኅሣሥ 08/2014 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
- Details
የዩኒቨርሲቲው የግብርና ሳይንስ ኮሌጅ በጋሞ ዞን ገረሴ ዙሪያ ወረዳ የእንስሳት መኖ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እና የአፈር ለምነትን መጠበቅ ላይ የሚሠራ የምርምር ሜጋ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ታኅሣሥ 09/2016 ዓ/ም በገረሴ ከተማ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡
Read more: አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በገረሴ ዙሪያ ወረዳ የ1.6 ሚሊዮን ብር የምርምር ሜጋ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ
- Details
Embassy of Canada in Ethiopia in collaboration with Arba Minch University hosted a day-long informative session on higher education opportunities in Canada for AMU academic staff and students on December 12, 2023. Click here to see more photos.
Read more: Canadian Embassy Briefs on Free Higher Education Opportunities in Canada
- Details
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በሳምንት መጨረሻ መርሃ ግብር በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የ2ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ተማሪዎች የልማታዊ ቡድን ሥልጠና ፕሮግራምን/Developmental Team Training Program /DTTP/ መሠረት በማድረግ በአርባ ምንጭ ከተማ ጉርባ ቀበሌ የአካባቢውን ማኅበረሰብና አጋር አካላትን በማስተባበር ያስገነቡት የደረቅ ቆሻሻ መጣያና ከጤና ተቋማት የሚወጡ የሕክምና ዕቃዎች ቆሻሻ ማቃጠያ (Incinerator) ታኅሣሥ 06/2016 ዓ/ም ተመርቆ ለማኅበረሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ
Read more: በዩኒቨርሲቲው የኅብረተሰብ ጤና 2ኛ ዲግሪ ተማሪዎች የተገነባው ፕሮጀክት ተመረቀ
- Details
በኮንትራት ውል መሠረት በደብዳቤ የተስተናገዳችሁ የቀድሞ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛና 3ኛ ዲግሪ ተመራቂዎች የቀድሞ ደብዳቤ ወደ ሰርተፊኬት እንዲቀየርላችሁ የቀረበ ጥያቄ በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል ውሳኔ ማግኘቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሠረት የምረቃ ደብዳቤው ወደ ሰርተፊኬት እንዲቀይርላችሁ የምትፈልጉ በሙሉ በእጃችሁ የሚገኘውን የቀድሞ ደብዳቤ ኮፒ በመመለስ ጊዜያዊ የትምህርት ማስረጃ (Temporary Certificate of Graduation) ከሰኞ ታኅሣሥ 15/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከሬጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክቶሬት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡