የጤና ሣይንስ ኮሌጅ ትኩረት የሚሹ የቆላማ አካባቢ በሽታዎች ምርምርና ስልጠና  ማዕከል ከአርባ ምንጭ ከተማ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለተወጣጡ ር/መ/ራንና መ/ራን እንዲሁም ለከተማው ጤና እና ውሃ ጽ/ቤት ባለሙያዎች የትምህርት ቤትና አካባቢው  ጤና፣ ትኩረት የሚሹ ቆላማ በሽታዎች፣ የተበከለ ውሃ ጉዳት፣ የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀም እንዲሁም የግልና የአካባቢ ንፅህናን በተመለከተ ከግንቦት 22-25/2009 ዓ/ም በኮሌጁ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ክፍል መምህር አቶ ደስታው ሀብቱ እንደገለጹት ስልጠናው በግልና በአካባቢ ንፅህና ላይ አዎንታዊ አመለካከትን የሚፈጥር ሲሆን በንፅህና ጉድለት ምክንያት በቆላማ አካባቢ የሚከሰቱ በሽታዎችን ሥርጭት ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት ግንዛቤ  ያስጨብጣል፡፡

በስልጠናው እንደተገለፀው ከንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረትና ከአካባቢ ንፅህና ጉድለት ጋር በተያያዙ በሽታዎች ምክንያት በየዓመቱ ከዓለማችን ህዘብ ከ1.6 ሚሊየን በላይ ለህልፈት ይዳረጋል፡፡ ትራኮማ፣ ጋንግሪን፣ የወስፋት በሽታ፣ የመንጠቆ ትል፣ ቢልሃርዚያና መሠል የተዘነጉ በሽታዎች የሚያስከትሉትን ጉዳት ለማስቀረት ግንዛቤ በማሳደግ፣ ምቹ የተማሪዎች መማሪያ አካባቢ በመፍጠር እና የግልና የአካባቢን ንፅህና በመጠበቅ ጤናማ ትውልድን ማፍራት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

የነበረባቸውን የእውቀትና የክህሎት ክፍተት ለመሙላት ስልጠናው ስልጠናው በቂ ግንዛቤ እንዳስጨበጣቸውና በቀጣይም ያገኙትን ክህሎት ለማህበረሰቡ በማካፈል ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር የበኩላቸውን እንደሚወጡ ሰልጣኞች ተናግረዋል፡፡