ማስታወቂያ ለነባር እና በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ነባር እና በ2010 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው እንኳን ለ2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት የትምህርት ዘመኑን  ሪፖርት  የማድረጊያ ቦታና የምዝገባ ጊዜያትን ከዚህ በታች በተገለፀው መሰረት እናሳውቃለን፡፡    

የምዝገባ ቀናት

ነባር 2ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ፣ የድህረ-ምረቃ እና የተከታታይና ርቀት ተማሪዎች ከመስከረም 22-24 /2010 ዓ.ም

አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች  ከመስከረም 27-29 /2010 ዓ.ም

አዲስ ያመለከታችሁ እና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የተከታታይና ርቀት ተማሪዎች ከመስከረም 29 - ጥቅምት 1፣ 2010 ዓ.ም

አዲስ ያመለከታችሁ እና የመግቢያ ፈተና ያለፋችሁ የመደበኛ እና የኤክስቴንሽን የድህረ-ምረቃ  ተማሪዎች ከመስከረም  29 -30/2010 ዓ.ም

ሪፖርት የማድረጊያ ቦታ

የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች…………………………….. በዋናው ካምፓስ

የህክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች   ……………………… በነጭ ሣር ካምፓስ

የተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች  ………………………………..በአባያ ካምፓስ

የግብርና ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ……………………………………በኩልፎ ካምፓስ

የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ እንዲሁም የማህበራዊ ሣይንስና ስነ-ሰብ  ኮሌጅ ተማሪዎች………በጫሞ  ካምፓስ

የፔዳጎጂ እና ብሄቨየራል ሳይንስ እንዲሁም የህግ ት/ቤት ተማሪዎች  ……………………….. በጫሞ  ካምፓስ

የሳውላ ካምፓስ ተማሪዎች   ………………………………………….. በሳውላ ካምፓሰ

ማሳሰቢያ፡ አዲስ የተመደባችሁ የዩኒቨርስቲው የቅድመ- ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው በምትመጡበት ወቅት፡-

የመሰናዶ ትምህርት (11ኛ እና 12ኛ ክፍል)  ትራንስክሪፕት ዋናውን ከ 2 ኮፒ ጋር

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውን ከ 2 ኮፒ ጋር

ሦስት በአራት የሆነ 4(አራት) ጉርድ ፎቶግራፍ

እንዲሁም ለግል መገልገያ የሚሆን እንደ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣  የስፖርት ትጥቅና የመሳሰሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡

@ ተማሪዎች በየካምፓሶቻችሁ  በተጠራችሁበት ቀናት ሪፖርት እንድታደርጉ እያሳሰብን ቀደም ብለው ወይም ዘግይተው ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት እንደማይሰጣቸው ያስታውቃል፡፡

@ ይህንን ማሳሰቢያ ተላልፈው በሚመጡ ተማሪዎች ላይ ለሚደርሰው መጉላላት ዩኒቨርስቲው ተጠያቂ አይሆንም፡፡

ለበለጠ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ድህረ-ገፅ  www.amu.edu.et ይመልከቱ፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እና አሉሙኒ ዳ/ጽ/ቤት