በሥልጠናው የውጤታማነት ትግበራ ስኬት አሠራር፣ ሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር፣ ሴኩላሪዝምና ህገ-መንግሥት እና የዩኒቨርሲቲው የ2010 ዓ/ም ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎቹ አጠቃላይ ኦሬንቴሽንም ተሰጥቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

ተማሪዎቹ ለዩኒቨርሲቲው አዲስ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የትምህርት ቆይታቸው በመከባበርና በመቻቻል ላይ የተመሠረተና ውጤታማ እንዲሆን ብሎም ህገ-መንግሥቱን በማክበር በሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር ትምህርት ተግባራዊነት ላይ ያላቸው ግንዛቤ እንዲዳብር ሥልጠናው የተዘጋጀ መሆኑን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሣይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ ጩፋሞ ገልፀዋል፡፡ ተማሪዎች ከቀለም ትምህርት ባሻገር የተስተካከለ አመለካከት ይዘው እንዲወጡ በሥነ-ምግባር ትምህርት አተገባበር ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባልም ብለዋል፡፡

የ1ኛ ዓመት የተፈጥሮ ሣይንስ ኮሌጅ ተማሪ ሮማን አየለ እና ተማሪ ተስፋ ዳንኤል ሥልጠናውን አስመልክተው በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው በዩኒቨርሲቲው የሚኖራቸው ቆይታ ስኬታማ እንዲሆን የሚያስችልና በጥሩ ሥነ-ምግባር ታንፀው እንዲመረቁ እገዛ የሚያደርግላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይም ሌላኛው የኮሌጁ ተማሪ ደስታ አባቡ በበኩሉ ሥልጠናው በዩኒቨርሲቲው በሚኖረው ቆይታ የሚገጥሙትን ፈተናዎች በሰከነ መንፈስ ከሌሎች ጋር በመሆን በመፍታት የትምህርት ጉዞውን ውጤታማ ለማድረግ እንደሚያስችለው ያለውን እምነት ገልጿል፡፡

5,833 አዲስ ገቢ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ሥልጠናውን በሁሉም ካምፓሶች ተከታትለዋል፡፡