የግብርና ሣይንስ ኮሌጅ የምርምር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በመምህራን የተሠሩ 18 የምርምር ንድፈ ሀሣቦችን መጋቢት 19/2010 ዓ.ም አቅርቦ አስተችቷል፡፡

የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ይስሃቅ ከቸሮ ችግር ፈቺ የምርምር ንድፈ ሀሣቦችን ወደ ተግባር በመቀየር የምግብ ዋስትናን በዞናችን እንዲሁም በሀገራችን በማረጋገጥ ድህነትን ለመቀነስ የበኩላችንን እንወጣለን ብለዋል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ::

ኮሌጁ በዓመት 2 ጊዜ የመምህራንን የምርምር ንድፈ ሀሣቦች የሚገመግም ሲሆን በኮሌጁ በ2010 ዓ.ም ለተለያዩ የልማት ሥራዎች ከተመደበው 1.1 ሚሊየን ብር በጀት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ምርምር ላይ ማዋላቸውን ዲኑ ገልፀዋል፡፡

በፕሮግራሙ የእንስሳትና አሳ ሀብት ምርታማነትን በምርምር ማሻሻል፣ የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር፣ መስኖን በመጠቀም የሰብል ምርታማነትን መጨመር፣ የግብርና ግብይትና እሴት ሠንሰለትን ማሻሻል እና ብዝሃሀ ህይወት ለአየር ንብረት ያለው አስተዋጽኦ የምርምር ንድፈ ሀሣቦቹ ካተኮሩባቸው ነጥቦች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

በዕለቱ ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ከማህበራዊ ሣይንስ፣ ከተፈጥሮ ሣይንስ እና ከግብርና ሣይንስ ኮሌጆች የተወጣጡ 75 ታዳሚዎች ተገኝተዋል፡፡