ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4000 በላይ ተማሪዎች ሰኔ 23/2010 ዓ/ም አባያ ካምፓስ በሚገኘው  አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል፡፡ የሳውላ ካምፓስም ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን የራሱን ካምፓስ ተማሪዎች ሰኔ 24/2010 ዓ/ም በሣውላ ከተማ የሚያስመርቅ ይሆናል ፡፡

በዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ በሚመራ አብይ ኮሚቴና ሌሎች 11 ንዑሳን ኮሚቴዎች የምረቃው ዝግጅት በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ፡፡ በምረቃው ሥነ-ሥርዓት ላይ የክብር እንግዳ፣ተጋባዥ እንግዶች፣ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ አባላት፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ተመራቂዎች ይገኛሉ፡፡

በዕለቱ በአዳራሽ ውስጥ ሊፈጠር የሚችለውን መጨናነቅ ለመቅረፍ ሲባል የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ በፌስቡክ፣ በዩቲዩብ እና በየካምፓሱ በሚገኙ  ዲጂታል ሳይኔጅ ስክሪኖች በቀጥታ የሚተላለፍ ሲሆን የምረቃ ሥነ -ሥርዓቱን ሽፋን ለመስጠት በርካታ የግልና የመንግሥት የብሮድካስትና የህትመት ሚዲያዎች ጭምር እንደሚዘግቡ ይጠበቃል፡፡

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት