በዩኒቨርሲቲው የሳይኮሎጂ ት/ት ክፍል ከማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የማህበረሰብ አገልግሎት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ከአርባምንጭና ከጫሞ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ /ቤት እንዲሁም ከአባያ ሁለተኛ ደረጃ /ቤት ለተወጣጡ 270 ሴት ተማሪዎች ከሚያዚያ 24-25/2007 / የህይወት ክህሎት ሥልጠና ሰጥቷል፡፡

የሥልጠናው ዋነኛ ዓላማ ሴት ተማሪዎች በትምህርታቸው ስኬታማ እንዲሆኑ ማስቻል እና ሀሳባቸውን፣ ፍላጎታቸውንና መብታቸውን በነፃነት እንዲገልፁ ማድረግ መሆኑን የት/ ክፍሉ ተጠሪ እና የሥልጠናው አስተባባሪ አቶ አንተነህ ዓለም ገልጸዋል፡፡ በተጨማሪም ውጤታማ የሆነ የጊዜ አጠቃቀምና የአጠናን ዘዴን በተመለከተ በስልጠናው ተካቷል፡፡

ተማሪ ተስፋነሽ ከበደ የጫሞ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ /ቤት 9 ክፍል ተማሪ ስትሆን ስልጠናው በራስ የመተማመን ስሜት እንድታዳብር እንደረዳት እና በተለይም ሴት ተማሪዎች ለትምህርታቸው ትኩረት ሰጥተው በመከታተል ያላቸውን ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀሙ እንደሚረዳ ተናግራለች ፡፡

ጥራትና አግባብነት ያለው ትምህርት መስጠት፣ ተፈላጊና ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምሮችን ማካሄድ እንዲሁም ማህበረሰብ ተኮር የሆኑ ሥልጠናዎችና አገልግሎቶችን መስጠት ከዩኒቨርሲቲው አበይት ተልዕኮዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡