P { margin-bottom: 0.08in; direction: ltr; line-height: 106%; widows: 2; orphans: 2; }

የዩኒቨርሲቲው የደህንነት ክፍል ከጋሞ ጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ጋር በመቀናጀት ከ300 በላይ ለሚሆኑ የደህንነት ሰራተኞች ከግንቦት 4-6/2007 /ም ድረስ በግጭትና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናው የግጭት መንስኤዎች፣ አፈታትና መፍትሄዎች፣ የግጭት መነሻዎችን ማጣራት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችና ወቅታዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ ግንዛቤ ለማዳበር የተዘጋጀ ነው፡፡

በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር የቻለ ከበደ እንደገለጹት ማናቸውም የዩኒቨርሲቲው እንቅስቃሴዎች ከጸጥታ ጋር በተያያዘ አንዳች እንከን ሳይኖራቸው መልካም የመማር ማስተማር ሂደት እንዲጎለብት ማድረግ ይጠበቃል፡፡ ለዚህም ስኬት ይህን መሰል ስልጠናዎች መሰጠታቸው ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖራቸው ም/ፕሬዝደንቱ አክለዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ በሰጡት አስተያየት ሥልጠናው የደህንነት ሰራተኞች ከተግባራቸው አንፃር ራሳቸውን በመመልከት በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ኃላፊነት እንዲሰማው የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡