ለተግባር ልምምድ ለሚወጡ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ሰኔ 19/2007 ዓ.ም የህክምና ትምህርት ቤት ነጭ ኮት የማልበስ ፕሮግራም አዘጋጀ፡፡

ተማሪዎቹ ወደ ህክምናው ሙ በሚገቡበት ወቅት በመልካም የሙያ ሥነ-ምግባርና ብቃት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ የልምምድ ጊዜያቸው ትልቅ የሽግግር ምዕራፍ በመሆኑ ለዚህ ተልዕኮ እውቅና ለመስጠት ፕሮግራሙ መዘጋጀቱን የገለጹት በኮሌጁ የህክምና /ቤት ዲን / ታዲዮስ ኃይሉ ናቸው፡፡ ፕሮግራሙ ተማሪዎች የተጣለባቸውን ሀገራዊ አደራና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ፣ ሰብአዊነትን እንዲረዱ እንዲሁም የህክምናውን ዓለም በቀላሉ እንዲላመዱ የሞራል ማነቃቂያ የሚሆናቸው ነው ብለዋል፡፡

ባለፈው የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤቱ የእጅግ ከፍተኛ ማዕረግ ተሸላሚ የነበሩት ዶ/ር ተመስገን መለስ ለዕጩ ተመራቂዎቹ ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን በሚሰማሩበት ተቋም ውጤታማ ሆነው የተሻለ ልምድ እንዲገበዩ ቁርጠኛ፣ እጅግ ጠንቃቃና ታጋሽ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

አስተያየታቸውን የሰጡ ተማሪዎች በቀለም ትምህርት ያገኘነውን እውቀት በተግባር ለመፈተሸ በምንዘጋጅበት ወቅት የሙያው የክብር መገለጫ የሆነውን ነጭ ኮት በዩኒቨርሲቲው እውቅና መልበሳችን ልዩ የደስታ ስሜት ፈጥሮልናል ብለዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ መምህራንና ኃላፊዎች በፕሮግራሙ በመገኘትተማሪዎች ነጭ የህክምና ጋዎን የማልበስ ሥነስርዓት ያከናወኑ ሲሆን ዶ/ር ታዲዮስ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን በመሸለም ለተማሪዎች መልካም የተግባር ልምምድ ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡