በአራቱ የለውጥ ሥራ አመራር መሣሪያዎች ዙሪያ በ2008 በጀት ዓመት ጠንካራ ተግባራት ለመሥራት መዘጋጀቱን የተቋማዊ ለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ገልጿል፡፡
በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ፣ በውጤት ተኮር ሥርዓት፣ በካይዘን እና በትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ዕቅድ ተይዞ ወደ ትግበራ መገባቱን የለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳባልቄ ዳልጮ ገልፀዋል፡፡
በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በከፍተኛ ትምህርት የትኩረት መስኮች ላይ በተለይም በመማር ማስተማር ብቁና ችግር ፈቺ ዜጎችን ለመፍጠር ፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በምርምርና ስርጸት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር እመርታዎች ለማስመዝገብ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክቶሬቱ በዩኒቨርሲቲው የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ቀደም ሲል ይታዩ የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት ግልፀኛና ኃላፊነቱን በአግባቡ የሚወጣ የሲቪል ሰርቪስ ሠራዊት በመገንባት በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ ለውጡን ለማስቀጠል እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ የመከታተል፣ የመደገፍና የማብቃት ሥራዎችንም ይሠራል፡፡
በዩኒቨርሲቲ አምስቱም ግቢዎች 3,599 የትምህርት ልማት ሰራዊት አደረጃጀቶች የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ሂደቱን በማቀላጠፍ ውጤታማ ተግባራት በመፈፀም ላይ ያሉ ሲሆን ይህንንም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በለውጥ ሥራ አመራር መሣሪዎች ላይ በበጀት ዓመቱ በትኩረት  እንደሚሠራ ተገለፀ
በዩኒቨርሲቲው የተቋማዊ ለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት በአራቱ የለውጥ ሥራ አመራር መሣሪዎች ዙሪያ በ2008 በጀት ዓመት ጠንካራ ተግባራት ለመሥራት መዘጋጀቱን ዳይሬክቶሬቱ ገልጿል፡፡
በዩኒቨርሲቲው በመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ፣በውጤት ተኮር ሥርዓት ፣በካይዘን እና የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ ላይ አበረታች ሥራዎችን ለማከናወን በዕቅድ ተቀምጠው ተግባራት ተጠናክረው መከናወን ጀምረዋል፡፡አገራችን ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት የተለወጠ ተቋም በመፍጠር ከስትራቴጅክ ዕቅድ ዘመን ጀምሮ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ሥራን በተጠናከረ መንገድ በማስከድ ላይ ትገኛለች፡፡
ከዚህ አንጻር ሂደቱ እንዲያግዝ በሁሉም ተቋማት የለውጥ ሠራዊት በመግንባት የተለያዩ የለውጥ መሣሪያዎችን በመጠቀም ይህንኑ የሚመራ አካል በመፍጠር እንቅስቃሴ ከተጀመረ ውስን ጊዜያት ተቆጥረዋል፡፡ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲም ይህን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ በተቋማዊ ለውጥ ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት በኩል የለውጥ ፕሮግራሞችን በመለየትና በመንደፍ  ዋና ዋና ግቦችንና ተግባራት ላይ እቅድ አውጥቶ እየሠራ መሆኑን ዳይሬክተሩ አቶ ዳባልቄ ዳልጮ ተናግረዋል፡፡
ዕቅዱ የከፍተኛ ትምህርት የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን የትኩረት መስኮች ላይ በተለይም በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ምርምርና ስርጸት፣ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ፕሮግራሞችን በብዛትና በብቃት በማካሄድ ብቁና ችግር ፈቺ የሆኑ ዜጎችን መፍጠርና ማህበረሰቡ ከድህነትና ኃላ ቀሪነት አረንቋ የማላቀቅ ተግባራት መፈፀማቸውን የማረጋገጥ እንዲሁም አመራርና አስተዳደር ማስፈንን ከማሳካት አኳያ ትኩረት በማድረግ እንደሚሰራም  ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል፡፡ 
ዳይሬክቶሬቱ ዕቅዱ በዋናነት በለውጥ ሠራዊት ግንባታ ዝርዝር ተግባራት አፈጻጸም ሂደቱን በተሟላ ደረጃ ግልጽነት በመፍጠር ፣ወጥነት ያለውን ሲቪል ሰርቭስ ሠራዊት በሁሉም ክፍሎች በመገንባት ፣በተደራጀና በተቀናጀ ሁኔታ በዩኒቨርሲቲው ለውጡን ለማቀላጠፍና ለማስቀጠል እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ መከታተል፣መደገፍ ብሎም ማብቃት ላይ ቀደም ሲል ይታዩ የነበሩ ክፍተቶች ለመድፈን በበጀት ዓመቱ በትኩረት ይሰራል፡፡
በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሥር ባሉ አምስት ግቢዎች 3599 የትምህርት ልማት ሰራዊት አደረጃጀቶች የለውጥ ሠራዊት ግንባታ ሂደት በማቀላጠፍ ውጤታማ ተግባራት በመፈፀም ላይ ያሉ ሲሆን ይህንንም ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ጥረት እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡