የሀዘን መግለጫ

ወ/ሪት ብርቱካን ቡሣ ከአባታቸው ከአቶ ቡሣ ግዛው እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙአየሁ እሸቴ በኮንሶ ወረዳ ጥር 6/1972 ዓ/ም ወለዱ፡፡  የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሀይሌ ደጋጋ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም የ2ኛ  ደረጃ  ትምህርታቸውን  በአርባ  ምንጭ  2ኛ  ደረጃና  መሰናዶ  ት/ቤት ተከታትለዋል፡፡

ወ/ሪት ብርቱካን ቡሣ በሰው ሀብት አመራር የት/ት መስክ ከቅድስተ ማሪያም ዩኒቨርሲቲ  ኮሌጅ  በ2003  ዓ/ም  በ10+3  በዲፕሎማ  የተመረቁ ሲሆን  ግንቦት 5/1999 ዓ/ም  በዩኒቨርሲቲው  ቤተ-መጽሐፍትና  ዶክሜንቴሽን  በሠርኩሌሽን አቴንዳንትነት በኮንትራት ተቀጥረዋል፡፡ 
ከሰኔ  1/2005  ዓ/ም  ጀምሮ  በዚሁ  ክፍል  የመጽሐፍት  ግምጃ  ቤት  ሠራተኛ ሆነው  በማገልገል  ላይ  ሳሉ  በደረሰባቸው  ድንገተኛ  የመኪና  አደጋ  ህዳር 12/2009 ዓ/ም በተወለዱ በ36 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲያችን በወ/ሪት ብርቱካን ቡሣ ድንገተኛ ሞት የተሰማውን ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል !!

 

 

ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት