ዓለም ዓቀፍ የኤች አይ ቪ/ ኤድስ ቀን በድምቀት ተከበረ

የሁሉ ዓቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት ‹‹አሁንም ትኩረት ለኤች አይ ቪ መከላከል›› በሚል መሪ ቃል ዓለም ዓቀፍ የኤች አይ ቪ/ኤድስ ቀንን ከህዳር 15-22/2009 ዓ/ም በተለያዩ ፕሮግራሞች በደማቅ ሁኔታ አክብሯል፡፡


የበዓሉ ዓላማ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስለ ኤች አይ ቪ/ኤድስ በሽታ አስከፊነት ያለውን ግንዛቤ በማዳበርና መዘናጋትን በማስወገድ ሥርጭቱን ለመግታት ጥረት ማድረግ መሆኑን የሁሉ ዓቀፍ ሴክተር ዳይሬክቶሬት የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ባለሙያ አቶ መርክነህ መኩሪያ ገልፀዋል፡፡

 

 

በዓሉን አስመልክቶ በተዘጋጀው የፓናል ውይይት እንደተገለጸው የግንዛቤ ማነስ፣ ቸልተኝነት፣ ተገዶ መደፈር፣ የሴተኛ አዳሪዎችና የጎዳና ተዳዳሪዎች መበራከት፣ ህገ-ወጥ ውርጃ፣ የሺሻና ጫት ቤቶች መስፋፋት፣ የኢኮኖሚ ችግር፣ የአቻ ግፊትና መሠል ምክንያቶች ሥርጭቱ እንዲባባስ የሚያደርጉ በመሆኑ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡


የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛ የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ብሎም አድሎና መገለልን ለማስቀረት ዩኒቨርሲቲው ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት  የበለጠ መሥራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡


በዩኒቨርሲቲው ነፃ የኤች አይ ቪ የምክር አገልግሎትና የደም ምርመራ እንዲመቻች፣ ከቫይረሱ ጋር ለሚኖሩ የዩኒቨርሲቲው ሠራተኞች የትምህርት ዕድል እንዲፈጠር እንዲሁም ሥርጭቱን ለመግታት ሁሉ አቀፍ ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው፣ ከጋሞ ጎፋ ዞን ጤና መምሪያ፣ ከአርባ ምንጭ ከተማ ጤና አጠባበቅ ፅ/ቤትና ሌሎች ሴክተር መ/ቤቶች የተወጣጡ ተሳታፊዎችና ባለድርሻ አካላት በዓሉ ላይ ተገኝተዋል፡፡