በዩኒቨርሲቲው ‹‹የሥነ-ትምህርት እና ስነ-ባሕርይ ሣይንስ ትምህርት ቤት›› ተመሥርቷል፡፡

የሥነ-ትምህርት እና ስነ-ባሕርይ ሣይንስ ትምህርት ቤት አስተባባሪ የነበሩት አቶ መስፍን ባልጉ እንደተናገሩት ቀደም ሲል ሳይኮሎጂ እና የጎልማሶች ትምህርትና ማህበረሰብ ልማት በትምህርት ክፍል ደረጃ ተማሪዎችን ተቀብለው ሲያስተምሩ እንዲሁም የፔዳጎጂ ትምህርት ክፍል የተለያዩ የስልጠና ፕሮግራሞችን ሲያስተባብር ቆይቷል፡፡ ምስሎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ ::

በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ-ግብር አዳዲስ ትምህርት ክፍሎች እየተበራከቱና እየሰፉ በመምጣታቸው፣ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርት ክፍሎች በመከፈታቸው እና HDP፣ ADRC፣ ELIC፣ PGDT PGDSL ስልጠናዎችን የሚሰጡ ማስተባበሪያዎች በመካተታቸው በትምህርት ቤት ደረጃ እንዲመሠረት ተደርጓል፡፡

በትምህርት ቤት ደረጃ መመሥረቱ በየደረጃው በመምህርነት ሙያ ላይ ለሚገኙ የማስተማር ስነ-ዘዴ ክህሎት ለማስጨበጥ፣ የትምህርት ባለሙያዎችን አቅም ለማጎልበትና የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የማስተማር ስነ-ዘዴን የተሻለና ውጤታማ ለማድረግ፣ የስነ-ባህርይ ሳይንስ ማዕከል በማቋቋም ለዩኒቨርሲቲውና ለአካባቢው ት/ቤቶች አገልግሎት ለመስጠት የሚረዳ ነው፡፡

ትምህርት ቤቱ በዘንድሮ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበው የሚመጡ የPGDT ተማሪዎችን በመደበኛ መርሃ-ግብር ተቀብሎ የሚያስተምር ሲሆን ለቀጣይ ሦስት አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞችን ለማስጀመር ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቋል፡፡ ትምህርት ቤቱ አዳዲስ የሚከፈቱትን ጨምሮ በአጠቃላይ አምስት ትምህርት ክፍሎችና አምስት የማስተባበሪያ ጽ/ቤቶችን ሲይዝ ለሦስት መምህራን በዘንድሮው ዓመት የፒ ኤች ዲ ትምህርት ዕድል ሰጥቷል፡፡