የ2010 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

የዩኒቨርሲቲው የ2010 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የስራ ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ሐምሌ 20/2010 ዓ/ም ተካሂዷል፡፡
የስትራቴጂክ ዕ/ዝ/ት/ግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገዝሙ ቀልቦ ባቀረቡት የማጠቃለያ ሪፖርት በትምህርት ጥራትና በመማር ማስተማር፣በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ በመልካም አስተዳደርና በቢዝነስና ልማት ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝርና ያጋጠሙ ችግሮች  ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

Read more: የ2010 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

 

ክፍት የሥራ መደብ ማስታወቂያ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀጥሎ በተገለፁት ክፍት የሥራ መደቦች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን  አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡ Click here to download the vacancy announcement.

ዩኒቨርሲቲው ከምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ጉጂ ዞን እና በደቡብ ክልል የጌዴኦ ዞን ህዝቦች መካከል በቅርቡ በተከሰተው ግጭት ሳቢያ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸው ይታወቃል፡፡  በመሆኑም ከዩኒቨርሲቲው  400 ፍራሾችና 2000 የመመገቢያ ሳህኖች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተሰበሰቡ  የተለያዩ አልባሳትና ጫማዎች ድጋፍ ሐምሌ 22/2010 ዓ/ም ለተፈናቃዮቹ ተሰጥቷል፡፡

Read more: ዩኒቨርሲቲው ከምዕራብና ምሥራቅ ጉጂ ዞን ለተፈናቀሉ ወገኖች የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

 

ማሳሰቢያ

አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2010 ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመለከታችሁ ተወዳዳሪዎችን የማጣራት ሥራ በማጠናቀቅ ለፅሑፍ ፈተና ጥሪ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ በቀድሞው ማስታወቂያ 2.75 የመመረቂያ ነጥብ ለወንዶችና 2.5 የመመረቂያ ነጥብ ለሴቶች ኑሯችሁ ለሌክቸራርነት እንዲሁም 2.5 እና ከዚያ በላይ ኑሯችሁ ለቴክኒካል አሲስታንትነት አመልክታችሁ ለፅሁፍ ፈተና ያልተጋበዛችሁ (Not Selected) የሆናችሁትን እንዳላችሁ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ በየዘርፉ የተጠቀሰውን አነስተኛ መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ የፅሁፍ ፈተናውን ሐምሌ 26፣ 2010 ዓ/ም በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመገኘት እንድትወስዱ ማሻሻያ የተደረገ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ማስታወቂያ

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2010 ባወጣው የቅጥር ማስታወቂያ መሠረት ለውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመለከታችሁ  ተወዳዳሪዎችን የማጣራት ሥራ የተጠናቀቀ ስለሆነ ለፈተና ያለፋችሁ ተወዳዳሪዎች ለፅሑፍ ፈተና ሐምሌ 26፣ 2010 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እንድትገኙ ያሳስባል፡፡