Print

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኦንላይን የመራጮች ምዝገባ ስርዓትን የዘረጋው የመራጮች ምዝገባ በሚካሄድበት ወቅት የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ፣ ነገር ግን በድምፅ መስጫ ዕለት የትምህርት ዘመኑ መጨረሻ ስለሚሆን ድምፃቸውን በቋሚ መኖሪያቸው (የመኖሪያ አድራሻቸው) ለሚሰጡ ተማሪዎች የመራጮች ምዝገባ እንዲካሄድ ለማስቻል ነው።


አንድ ተማሪ በኦንላይን ለመመዝገብ የሚከተሉት ሁኔታዎች መሟላት አለበት፡

    የኢንተርኔት አገልግሎት መኖር አለበት
    ላፕቶፕ ወይም ሞባይል ስልክ ሊኖር ይገባል
    የመራጮችን ምዝገባ ለማጠናቀቅ መጫን ያለበትን የተማሪ መታወቂያ ካርድ ስካን አድርጎ ማዘጋጀት አለበት
    በቋሚነት በሚኖርበት አድራሻው መሰረት ድምፅ ለመስጠት የሚመዘገብበትን የምርጫ ጣቢያ ስም ማወቅ አለበት።
    የሁሉንም የምርጫ ጣቢያዎች ስም ከዚህ ድረ ገጽ ማግኘት ይቻላል፡ www.nebe.org.et. ተማሪው ከቋሚ የመኖሪያ አድራሻው አቅራቢያ የሚገኘው የምርጫ ጣቢያ ስምን በተመለከተ እርግጠኛ ካልሆነ፣ ለምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልል ጽ/ቤት፣ ለቤተሰቦቹና ለጎረቤቶች ጥያቄ አቅርቦ መረዳት ይችላል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ፋይል ይመልከቱ

ኦንላይን የመራጮች ምዝገባ ስርዓት መምሪያ