የዩኒቨርሲቲው የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ባዮሎጂ ትምህርት ክፍል በ‹‹Biodiversity Conservation and Management›› የትምህርት ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ በ3ኛ ዲግሪ ለማስመረቅ የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ አጠናቋል፡፡ ዕጩ ተመራቂ ሙላቱ ኦሴ ለምረቃ ብቁ የሚያደርገውን ጥናታዊ ጽሑፍ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገራት እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ምሁራን በተገኙበት ሰኔ 04/2013 ዓ/ም አቅርቧል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ጥናታዊ ጽሑፉ ‹‹Habitat Fragmentation Effects on vascular Epiphytes, Bryophytes and predator-pest Dynamics in Kafa Biosphere Reserve and Nearby Coffee Agro ecosystem, South West Ethiopia›› በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሲሆን በከፋ ዞን የሚገኝ ጥብቅ ደን ውስጥ የሚገኙ አነስተኛ ዕፅዋት ለሥነ ምኅዳሩ ያላቸው ጠቀሜታና በአርሶ አደሩ ላይ የሚያስከትሉት የጎንዮሽ ጉዳት ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ ጥናቱ ችግሩን በማቃለል አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረግ የሚቻልበትን መንገድም ይጠቁማል፡፡

ተመራቂው ለምረቃ የሚያበቁትን ቅድመ ሁኔታዎች በሙሉ ማሟላቱን የገለጹት የኮሌጁ ዲን ዶ/ር ፈቃዱ ማሴቦ ኮሌጁ በ3ኛ ዲግሪ ሲያስመርቅ የመጀመሪያው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር ዓለማየሁ ጩፋሞ በበኩላቸው ዕለቱ በዩኒቨርሲቲው ታሪክ ትልቅ ትርጉም ከሚሰጣቸው ቀናት መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ዩኒቨርሲቲው የምርምር ዩኒቨርሲቲ ሆኖ እንደመለየቱ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ማስመረቅ መጀመሩ ወደ ፊት መድረስ ለምናልመው ራዕይ ስኬት ትልቅ መነሻና ልምድ የምናገኝበት ነው ብለዋል፡፡

ዕጩ ተመራቂ ዶ/ር ሙላቱ ኦሴ በዩኒቨርሲቲው የነበረው ቆይታና የደረሰበት ስኬት አስደሳች መሆኑን ገልጾ በሃሳብና በተለያዩ መንገዶች ለደገፉት ቤተሰቦቹ፣ ለመምህራኑና ለጥናታዊ ጽሑፉ አማካሪዎች ላቅ ያለ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት