በ2013 የትምህርት ዘመን በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ ተማሪዎች ሰኔ 28 እና 29 ሪፖርት የሚደረግበት፣ ሰኔ 30 እና ሐምሌ 01 የምዝገባ ቀናት እንዲሁም ሐምሌ 05/2013 ዓ/ም መደበኛ ትምህርት የሚጀመርበት በመሆኑ ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡-

  1. የ8ኛ፣ 10ኛ እና የመሠናዶ ትምህርታችሁን ያጠናቀቃችሁበት ውጤት ሰርተፍኬት ዋናውና ፎቶ ኮፒ፣
  2. ከ 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪፕት ዋናውና ፎቶ ኮፒ፣
  3. አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስና የስፖርት ትጥቅ፣
  4. ስምንት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶ እና
  5. ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ይዛችሁ እንድትመጡና

በጉዞ ወቅትም ኮቪድ-19ን ለመከላከል በተገቢ ሁኔታ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳወቅን ከላይ ከተጠቀሱ ቀናት ውጭ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት