Print

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድባችሁ ለነበራችሁና በአሁኑ ሰዓት በጊዜያዊነት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የ2013 ዓ/ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 08 እና 09/2013 ዓ/ም መሆኑን እያሳወቀ ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡-

  1. የ8ኛ፣ 10ኛ እና የመሠናዶ ትምህርታችሁን ያጠናቀቃችሁበት ውጤት ሰርተፍኬት ዋናውና ፎቶ ኮፒ፣
  2. ከ 9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበት ትራንስክሪፕት ዋናውና ፎቶ ኮፒ፣
  3. አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስና የስፖርት ትጥቅ፣
  4. ስምንት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶ እና
  5. ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችል የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል (ማስክ) ይዛችሁ እንድትመጡ እንዲሁም በጉዞ ወቅትም ኮቪድ-19ን ለመከላከል ተገቢ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እያሳሰበ ከተጠቀሱ ቀናት ውጭ ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ይገልጻል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ