በሳይንስና ክፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሐምሌ 5-8/2013 ዓ/ም እየተካሄደ በሚገኘው የትምህርት፣ የምርምር፣ የቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ኮንቬንሽን ላይ የተለያዩ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ሥራዎች እና ወደ ማኅበረሰብ የወረዱ የምርምር ፕሮጀክቶችን በማቅረብ እየተሳተፈ ይገኛል፡፡  ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

ኮንቬንሽኑ የሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለባለድርሻ አካላት ለማስተዋወቅና በከፍተኛ ትምህርት፣ በቴክኒክና ሙያ ተቋማትና በኢንዱስትሪው ዘርፍ መካከል ለምርምርና ቴክኖሎጂ ልማት እንቅስቃሴ የሚያግዙ የእርስ በእርስ ትስስርና ቅንጅታዊ አሠራር እንዲጠናከር ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ምንስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ተናግረዋል፡፡

የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ክብርት ሣህለወርቅ ዘውዴ መሰል የምርምርና የፈጠራ ኤግዚብሽኖች መደረጋቸው ተሰጥዖ ያለቸውን የፈጠራና የምርምር ሰዎችን ከማበረታታትና ከማስተዋወቅ እንዲሁም የምርምርና የፈጠራ ሥራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር ጉልህ ፋይዳ ይኖራቸዋል ብለዋል፡፡ በጉብኝታቸው ወቅትም ያዩዋቸውን የፈጠራና የምርምር ሥራዎች አበረታች መሆናቸውን ተገንዝቤያለሁ ብለዋል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ዳምጠው ዳርዛና የልዑክን ቡድኑን በመምራት በሥፍራው የተገኙት የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ ዩኒቨርሲቲው በኮንቬሽኑ ላይ በርካታ የምርምር፣ የፈጠራና ወደ ማኅበረሰቡ የወረዱ ፕሮጀክቶችን ይዞ መቅረቡን ተናግረው ጉባዔው በዩኒቨርሲቲዎች መካከል የልምድ ልውውጥ እንዲኖር በማድረግ እንዲሁም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በኢንዱስትሪዎች መካከል ትስስር ከመፈጠር አንፃር ፋይዳው ጉልህ ነው ብለዋል፡፡

በኮንቬንሽኑ ላይ 36 የመንግስትና የግል ዩኒቨርሲቲዎች እና 31 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት