Print

የሃይድሮሊክስና ውሃ ሀብት ምኅንድስና ፋከልቲ ከኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ ለመጡ መምህራን የቤተ-ሙከራ ዕቃዎች አያያዝ፣ አጠቃቀምና አስተዳደርን በተመለከተ ከሰኔ 07-11/2013 ዓ/ም ሥልጠና ሰጥቷል፡፡   ፎቶዎቹን ለማየት እዚህ ይጫኑ

የሃይድሮሊክስና ውሃ ሀብት ምኅንድስና ፋከልቲ ዲን አቶ መልካሙ ተሾመ እንደገለጹት የቤተ-ሙከራ ሥራዎች ላይ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሲነፃፀር የተሻለ ልምድ ያለው ስለሆነ አዳዲስና ጀማሪ ዩኒቨርሲቲዎችን ለማሳደግና ለማብቃትና ባለው ሀብት በጋራ ተደጋግፎ ለመሥራት ሥልጠናው ተዘጋጅቷል፡፡

የውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ሳሙኤል ዳጋሎ በበኩላቸው የሃይድሮሊክስና የሲቪል ምኅንድስና ቤተ-ሙከራዎች ለመማርና ለምርምር ሥራዎች መሠረታዊና አስፈላጊ በመሆናቸው በዘርፉ ያለውን የቤተ-ሙከራ አጠቃቀም ማሳየትና ማሳወቅ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

የሥልጠናው ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ዩኒቨርሲቲያቸው ጀማሪ ከመሆኑ አንፃር ሥልጠናው በጣም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው መሰል ሥልጠናዎችና የጋራ ግንኙነቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል፡፡

የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት