የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፕሮግራም በሀገር በቀል የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ቀጥሎ በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

  1. PhD in Groundwater Engineering
  2. PhD in Irrigation Engineering
  3. PhD in Water Supply and Sanitary Engineering

በመሆኑም ከላይ በተጠቀሱት የ3ኛ ዲግሪ የትምህርት መስኮች መማር የምትፈልጉ እስከ ሃምሌ 23/ 2013 ዓ/ ም ድረስ ለአዲስ አበባ እና አከባቢው ለምትገኙ አመልካቾች አዲስ አበባ በሚገኘው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ቢሮ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ቢሮ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

የፈተና ጊዜ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል፡፡

ፈተናዉን አልፈው ፕሮግራሙን ለሚቀላቀሉ ተማሪዎች የመኝታ አገልግሎት እና መሰል የምርምር ድጋፎችን ዩኒቨርሲቲው እንደሚሰጥ እንገልጻለን።