Print

ʻʻኢትዮጵያን እናልብሳት!ʼʼ በሚል መሪ ቃል ሐምሌ 20/2013 ዓ/ም ከጧቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በአርባ ምንጭ ከተማና አካባቢው በአንድ ቀን 100 ሺህ ችግኞችን ለመትከል የተያዘውን ዕቅድ ከከተማውና አካባቢው ማኅበረሰብ ጋር ለማሳካት በቤሬ ተፋሰስ እንዲሁም የፊታችን ዓርብ ሐምሌ 23/2013 ዓ/ም ʻʻGreen Legacy, Green Campus!” በሚል መሪ ቃል ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በሁሉም የዩኒቨርሲቲው ካምፓሶች 3ኛው አገራዊ የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ይካሄዳል፡፡

ስለሆነም የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ በሙሉ በንቃት በመሳተፍ በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በመገኘት የ3ኛውን ዙር አገራዊ ጥሪ ምላሽ በመስጠት አረንጓዴ ዐሻራውን እንዲያስቀምጡ ዩኒቨርሲቲው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ