Print

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ቤት በ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ፣ በማታ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር መስፈርቱን የሚያሟሉ አዲስ አመልካቾችን ከዚህ በታች በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መረጃዎች

  1. ሙሉ የትምህርት መረጃ ኦርጅናልና ሁለት(2) ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ሁለት(2) ጉርድ ፎቶግራፍ
  2. የአመልካቹን ጥንካሬና ባህሪ የሚገልጽ ከመ/ቤት ኃላፊ /ከቀድሞ መምህር/ የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ /Recommendation Letter/
  3. በመንግሥት/በድርጅት ስፖንሰርነት ለሚማሩ በመሥሪያ ቤቱ/ በድርጅቱ ኃላፊ የሚፈረም/Sponsor hip Form/ ከዩቪርሲቲው ድረ-ገፅ www.amu.edu.et ማግኘት ይችላል፡፡
  4. የመመዝገቢያ ክፍያ የ100 ብር ደረሰኝ በመያዝ የማመልከቻ ቅጽ ከተማሪዎች ምዝገባና ቅበላ ክፍል ቢሮ ቁጥር 210፣ 211 እና ከዩቪርሲቲው ድረ-ገፅ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የማመልከቻ፣ የፈተና መስጫ፣ የውጤት ማሳወቂያ፣ የምዝገባ ጊዜና ቦታ

ማሳሰቢያ፡-

  1. ማንኛውም የመግቢያ ፈተና ያለፈ አመልካች ኦፊሻል ትራንስክሪፕት /Official Transcript/ ብቻል በምዝገባ ወቅት ካልሆነ በ60 ቀናት ውስጥ ካልቀረበ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ በጥብቅ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
  2. በአካል ቀርባችሁ ማመልከት ለማትችሉ አመልካቾች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000021480502 የማይመለስ 100 ገቢ ያደረጋችሁበት ደረሰኝና ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒ/ስካን በማድረግ በኢ-ሜይል አድራሻችን This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
  3. የትምህርት ፕሮግራሞች ዝርዝር በዩኒቨርሲቲው ዌብሳይት፣ ፌስቡክና ቴሌግራም ቻናል የተቀመጠ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የአርባ ምንጭ ዩንቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት